ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መድሃኒት በህግ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተያዘ

የኢትዮጵያ የምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እንዳስታወቀዉ፤ በሞያሌ ከተማ በአራት መድሃኒት ቤቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ ግምታቸዉ 4 4 ሚሊዮን 2 መቶ 14 ሺህ ብር በላይ የሚሆኑ ህገወጥ መድሃኒቶችን በቁጥጥር ስራ አዉያለሁ ብሏል፡፡

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን አብርሃም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት፤ መድሃኒቶቹ ጥራታቸዉ ያልተረጋገጠ እና ያልተመዘገቡ መሆናቸዉን ገልፀዋል፡፡

4ቱ መድሃኒት መደብሮችም እርምጃ እንደተወሰደባቸዉ የተገረ ሲሆን ህገ ወጥ መድሃኒቶችም በመወገድ ላይ ናቸዉ ተብሏል፡፡

እነዚህ ህገ ወጥ መድሃኒቶች በጉምሩክ ሰራተኞች፤በፖሊስ ኮሚሽን እና በአካባቢዉ ህብረተሰብ አማካኝነት መያዘቸዉን ያስታወቁት አቶ ሳምሶን ህብረተሰቡ ህገወጥ መድሃኒቶን እንዲከላከል አሳስበዋል፡፡

ዘገባው የአባቱ መረቀ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *