የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ጨምሮ የጮኬና ጉና ተራሮችን ለማልማት 15 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ

የአማራ ከልል የተፈጥሮ ሀብት ልምትና ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ጌታቸዉ እንግዳየሁ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ጨምሮ የጉና እና የጮኬ ተራሮችን በክረምቱ ወቅት ለማልማት 15 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የባለስልጣኑ ተናግረዋል፡፡

በጀቱን ከፌደራል መንግስት ለማግኘት ጥያቄ ማቅረባቸዉን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ምላሽ እንዳገኙ ወደ ስራ እንደሚገቡም ገልፀዋል፡፡

እነዚህ ቦታዎች በደረሰባቸዉ አደጋዎች በመራቆታቸዉ የመልሶ ማልማት ስራ ማስፈለጉም ታዉቋል፡፡

15 ሚሊዮን ብሩ ለችግኘ ተከላ እና ለሌሎች ተያያዥ ስራዎች እንደሚዉል አቶ ጌታቸዉ ለጣቢያችን አስታዉቀዋል፡፡

የአማራ ከልል የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን በክረምቱ ከ1 ቢሊዮን ችግኝ በላይ ለመትከል ማቀዱን የገለፀ ሲሆን በምዕራብ አማራ ችግኝ ተከላው ተጀምሯል ብለዋል።

በአባቱ መረቀ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *