ግምታዊ ዋጋው 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ምስርበቁጥጥር ስር ዋለ

ግምታዊ ዋጋው 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ምስር በኮንትሮባንድ መንግድ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ዋለ

ኮድ 3 A01039 ኢት የሆነ ሲኖትራክ ተሸከርካሪ 200 ኩንታል ምስር ጭኖ ከባሌ ዞን ራይቱ ከሚባል አካባቢ ወደ አዳማ በማቅናት ላይ እያለ ሳዊና ወይም ጊነር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ላይ ፣ ኮድ 3 35819 አ.አ የሆነ ኤፍ ኤሳር (FSR) 99 ኩንታል ምስር ጭኖ እንዲሁም ኮድ 3 A60315 አ.አ የሆነ ኤፍ ኤሳር (FSR) 97 ኩንታል ምስር ጭኖ ሲንቀሳቀስ አዳባ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ መያዛቸውን የሀዋሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በቁጥጥር ሰር ሊውሉ የቻሉት በጉምሩክ ሰራተኞችና በፌደራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት የጋራ ጥረት መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሲኖ ትራኩ ላይ የነበሩት ተጠርጣሪዎች ተሽከርካሪውን አቁመው ለጊዜው ሲሰወሩ ከኤፍሳሮቹ ላይ የነበሩ 3 ተጠርጣሪዎች ግን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

ይሁንና ምስሩ እንዴት ህገወጥ ሊሆን እንደቻለ ለማጣራት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ምንጭ ገቢዎች ሚኒስቴር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *