የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ፒንግ ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ለመመካከር ወደ ሰሜን ኮሪያ አቀኑ

ይህም ከ14 ዓመት በኋላ ሰሜን ኮሪያን የጎበኙ የመጀመሪያው ቻይና መሪ አድርጓቸዋል፡፡

ላለፉት 14 ዓመታት አንድም የቻይና መሪ ወደ ሰሜን ኮሪያ አምርቶ የማያውቅ ሲሆን ፕሬዝዳንት ሺም ስልጣን ላይ ከወጡበት ከ2012 ወዲህ ያደረጉት የመጀመሪያው ጉብኝት ሆኗል።

ሁለቱ መሪዎች በቻይና አራት ያህል ጊዜ ተገናኝተዋል፡፡በዚህ ጉብኝት በሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ፕሮግራም ዙሪያና ኢኮኖሚያዊ ጎዳዩች ላይ ይመክራሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡

የፕሬዝዳንት ሺ ጉብኝት የተሰማው የቡድን 20 ሀገራት ስብሰባ በጃፓን ከመካሄዱ ከሳምንት በፊት ነው።

ምዕራባዊያን አገራት ፊት የነሷት ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የኢኮኖሚ ማዕቀብ የተጎዳው ኢኮኖሚዋን ሊያሳድግ የሚችል የንግድ ስምምነት ከቻይና ጋር እንደምትፈራረም ይጠበቃል።
በአሜሪካ ጋር የንግድ ጦርነት የተከፈተባት ቻይና ከኒውክሌር አረር ተሸካሚዋ ሰሜን ኮሪያ ጋር ልታደርገው ያሰበችው አዲስ ወዳጅነት የዓለም ትኩረትን ስቧል።

ፕሬዝዳንቱ በጃፓን ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ይመክራሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባለፈው ሳምንት የቻይናው ፕሬዝደንት በጃፓኑ የቡድን ሀያ ሀገራት ጉባኤ ላይ ፕሬዝደንት ሺ መቅረት አይችሉም ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ይህ የሺ እና የኪም ውይይት በሀኖይ ትራንፕና ኪም ያልተሳካ ውይይት ከተካሄደ በኃላ የተደረገ የመጀመሪያው ውይይት ይሆናል ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡

በያይኔአበባ ሻንበል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *