የሳዑዲ ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን በጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ እጃቸው አለበት ተባለ

የመንግሥታቱ ድርጅት ልዩ መረጃ የጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያን በተመለከተ ይፋ ባደረገው ሪፓርት የሳውዲ ዓረቢያ ልዑል በግድያው እጃቸው እንዳለበት የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አለኝ ነው የሚለው፡፡

ሳውዲ ዓረቢያ መንግስት በበኩሉ የተባበሩት መንግሥታት አለኝ የሚለውን መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ሲል አጣጥሎታል፡፡

ይፋ በተደረገው አዲስ መረጃ የሳውዲ ዓረቢያ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን ጥፋተኛነታቸውን ለማረጋገጥ ግን ተጨማሪ ምርመራ መደረግ እንዳለበት ጠቅሷል።

የመንስታቱ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሃለፊ አኘስ ካላማንድ ልዑል የግል ንብረት ዓለም አቀፍ ማእቀብ እንዲጣልበት መጠየቃቸውን ባልደረባችን ያይኔአበባ ሻንበል ሲ ኤን ኤንን ዋቢ አድርጋ ዘግባለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *