የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ለንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት የሚውል የ8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብድር ሰጠ

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ለአካባቢ ፅዳት እና ለጤና አጠባበቅ የሚውል 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

የብድር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ሚስ ካሮሊን ተርክ ተፈራርመውታል፡፡

ፕሮጅክቱ ተግባራዊ ሲደረግ 3 ሚሊዮን የሚሆን በገጠር እና በከተማ የሚኖር ህዝብን የንፁህ ውሃ አቅርቦት፣በአካባቢ ፅዳትና በጤና አጠባበቅ ላይ በሚሰሩ ስራዎች ተጠቃሚ ይሆናል፡፡

በስምምነቱ ወቅት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እንደተናገሩት ብድሩ (One Wash) ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል ነው፡፡

ፕሮጅክቱ ሲጠናቀቅ በከተማ እና በገጠር የንፁህ የውሃ አቅርቦትና የአካባቢ ጥበቃ ላይ መሻሻሎች እንዲኖሩ ያደረጋል ብለዋል፡፡

የዓለም ባንክ በኢትዮጲያ ዳይሬክተር ሚስ ካሮሊን ተርክ በበኩላቸው እንደገለፁት ብድሩ በሁለተኛው የእድገት ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ በንጹህ ውሃ አቅርቦትና በአካባቢ ፅዳት ለሚከናወኑ ስራዎች ድጋፍ የሚውል ነው ብለዋል፡፡

የዓለም ባንክ በሚቀጥሉት ዓመታትም በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች የሚያደረገው ድጋፍ አጠክሮ እንደሚቀጥል ዳይሬክተሯ ጨምረው ተናገረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት ከ29 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ እዳ እንዳለባት ይታወቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *