የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ገቢ በ196 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳየ

አገሪቱ ባለፉት 11 ወራት ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳ ነበር።

ይሁንና በተጠቀሰው ወራት ውስጥ የተገኘው ገቢ 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ወይም የእቅዱ 61 በመቶ ብቻ መሳካቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የወጪ ንግድ አፈፃፀም ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ196.8 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቷል፡፡

ታንታለም፣ የጥራጥሬ ሰብሎች እና የቅባት እህሎች ከእቅድ በላይ ገቢ ካስገኙት የባህርዛፍ እና ጫት ንግድ በመቀጠል የተሻለ ገቢ አስገኝተዋል ተብሏል፡፡

ከተያዘላቸው ዕቅድ ከ50% እስከ 74% ክንውን ያስመዘገቡ ምርቶች ደግሞ ቡና፣ ኤሌክትሪክ፣ አበባ፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ አልባሳት፣ ዓሣ፣ ሻይ ቅጠል፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ሥጋ ናቸው።

ቅመማቅመም፤ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፤ የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን፤ ምግብ መጠጥና ፋርማስዩቲካል፤ የስጋ ተረፈ ምርት፤ የቁም እንስሳት፤ ማዕድን፣ የብርዕና አገዳ ምርቶች ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ማስገኘታቸውን ባልደረባችን ሳሙኤል አባተ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *