ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ እንዲወሰድ ያስተላለፉትን የአጸፋ እርምጃ መሰረዛቸው ተነገረ

ኢራን በትናንትናው ዕለት የአሜሪካን ሰው አልባ አውሮፕላን መታ መጣሏን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ከባድ ስህተት መፈጸሟን ተናግረው ነበር፡፡

የኢራኑ የውጨ ጉዳይ ሚኒስትር ጃቫድ ዛሪፍ አሜሪካ የአየር ክልላችንን ጥሳለች ለዚህም ልትጠየቅ ይገባታል ብለዋል፡፡

አሜሪካ በበኩሏ አለም አቀፍ የአየር ክልል ውስጥ ነው ሰው አልባ አውሮፕላኔ ተመቶ የወደቀው ስትል ኢራንን ከሳለች፡፡

ይህን ተከትሎም ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ላይ ጥቃት ለመፈጸም ትእዛዝ አስተላልፈው እንደነበር ኒው ዮርክ ታይምስ አንድ የኋይት ሃውስ ባለስልጣንን ጠቅሶ አስነብቧል፡፡

የውጊያ አውሮፕላኖችና መርከቦች ቦታቸውን ይዘው የነበረ ቢሆንም የተተኮሰ ሚሳኤል አለመኖሩን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

ይሁንና ፕሬዘዳንት ትራመፕ በኢራን ላይ የአጸፋ አርምጃ እንዲወሰድ ከወሰኑ በኋላ ለምን ውሳኔያቸውን እንዳጠፉ እስካሁን አልተገለጸም።

በአባይነሽ ሽባባው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *