መንግስት በኢኮኖሚ ያደግንበትን ቁጥር ከመናገር በዘለለ የህዝቡ የኑሮ ብሶት ላይ መስራት እንደሚገባ ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ተናገሩ

ፓርቲው የቀደመው ኤህአዴግም ቢሆን በኢኮኖሚው ማደጋችንን የሚያሳዩ አማላይ ቁጥሮች ይነግረን ነበር፤ ሆኖም በዕለተለት የህዝቡ ኑሮ ላይ እናይ የነበረው ተቃራኒውን ነበር ያለ ሲሆን አሁንም ያለው በተመሳሳይ በኑሮ ውድነት የሚያማርር ህዝብ ነው ብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በፓርላማ ተገኝተው በ2011 ዓ.ም ኢኮኖሚው 9 ነጥብ 2 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል ማለታቸውን አስመልክቶ የኦፌኮ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ስታትስቲክስ እንዳለ ሆኖ ህዝቡ በኑሮ ውድነት ያለው ብሶት ምን ያህል የከፋ እንደሆነ ስናይ አድገናል ተብሎ የሰማነው ቁጥር ፤ ቁጥር ብቻ ይሆንብናል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢኮኖሚው እያገገመ መሆኑ መናገራቸውም ፣ በኢኮኖሚው የተሸለ መንገድ ላይ ነው ያለነው ማለታቸውም በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ኑሮ ላይ የሚታይ ለውጥ አምጥቶ እስካላሳየን ድረስ እንደከዚህ ቀደሙ ኢህአዴግ ሁሉ ሪፖርታቸው ታአማኒነቱ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፡፡

ስለሆነም የህዝቡ የኑሮ ጥራት ላይ መንግስት የተሻለ ስራ ሊሰራ ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሔኒክ አሥራት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *