የኢትዮጵያ ቆዳ ንግድ የ26 ሚሊዮን ዶላር ጉድለት አሳየ

ሀገረቱ ባለፉት አስር ወራት ውስጥ ያገኘችው ገቢ 109 ሚሊዮን ዶላር ነው ይላል የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስትቲውት፡፡

የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር አቶ ብረሀኑ ሰርጃቦ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ሀገሪቱ ባለፈው አመት ከቆዳ ኢንዱስትሪ ኤክስፖርት 135 ሚሊየን ዶላር ገቢ ያገኘች ሲሆን በተያዘው ዓመት ግን 109 ሚሊየን ዶላር ብቻ ነው ማግኘት የቻለችው ፡፡

የቆዳ ኢንደስትሪው ዘርፍ እድገት ቀደም ሲል ከነበሩት ጊዜያት ጋር ሲነፃፀር ገቢው አሽቆልቁሏል፡፡

በዚህ ዓመት በተፈጠረው የአለም ገበያ መቀዛቀዝ በቆዳ ኢንደስትሪ የውጭ ንግድ ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተፅእኖ ቀላል እንዳልነበር አቶ ብርሀኑ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በሀገሪቱ የመብራት መቆራረጥና የቆዳ ጥራት ደረጃ ማነስ በዘርፉ የተጠበቀውን ያህል ገቢ ማግኘት እንዳላስቻለ ነው የሚያብራሩት፡፡

በአለም አቀፍ የቆዳ ምርት ገበያ ላይ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ ከውጭ የሚገኘውን ገቢ ከፍ ለማድረግ ከቻይና ፤ ሆንግ ኮንግ ፤ ጣሊያንና ህንድ ሀገራት በተጨማሪ ሌላ ገበያ የማስፋት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጻል፡፡

በደረሰ አማረ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *