ኢትዮጵያ በቀጣዩ ዓመትም የኤሌክትሪክ ሀይል እጥረት እንደሚያጋጥማት ተገለጸ

ኢትዮጵያ በ2012 ዓ.ም 16 ሺህ 165 ጂጋ ዋት እንደሚያስፈልጋት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሀገሪቱ በ2011 ዓ.ም የ13 ሺህ 835 ጂጋ ዋት ሰዓት ሀይል ለማቅረብ አቅዳ የነበረ ቢሆንም ግድቦች በውሃ እጥረት ምክንያት የሚፈለገውን ያህል ማምረት ባለመቻላቸው መብራት በፈረቃ ሲዳረስ ቆይቷል።

ይሁንን አገራዊ የሃይል ፍላጎቱ በ2012 ዓ.ም ወደ 16 ሺህ 1 መቶ 65 ጂጋ ዋት ሰዓት ወይም አሁን እየተገኘ ካለው ሃይል ተጨማሪ 8 ነጥብ 9 በመቶ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

የውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ እንዳሉት 254 ሜጋ ዋት ሀይል የሚያመነጨው የገናሌ ዳዋ ግድብ 3 ከአንድ ወር በኋላ ይመረቃል።

በተጨማሪም 125 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው የአይሻ ፀሀይ ሀይል ማመንጫ ጥር ወር ላይ ሀይል ወደ ማመንጨት ስለሚሸጋገር ተጨማሪ ሃይል እናገኛለን የሃይል እጥረቱም ይፈታል ብለዋል።

ዘገባው የደረሰ አማረ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *