የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት 100 ሺህ ቤቶችን እንደሚገነባ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት በ2012 አንድ መቶ ሺ ቤቶችን የመገንባት እቅድ እንዳለው እና ይህንኑ ፕሮጀከት ሀምሌ 4 ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የቤቶቹ ግንባታ አንድ ሺ የግል ይዞታዎች ላይ እንደሚከናወንም ተሰምቷል፡፡

ይዞታዬን አጋራለሁ ከተማዬንም አለማለው የሚለውን ፅንሰ ሀሳብ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመስጠትም ፕሮጀክቱ ይፋ ለማድረግ በስካይላይት ሆቴል ሀምሌ 4 ቀጠሮ ይዟል፡፡

በዚህ ፕሮግራም ላይም ከግል ባለይዞታዎች የተሰበሰቡ የካርታ እና ፕላን ስምምነቶችም ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮው ጋር ርክክብ ይፈፅማሉ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ሀላፊ ፣ የከተማና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ፣ የባንክ ሀላፊዎች፣ ይዞታቸውን ለፕሮጀክቱ የሰጡ የግል ባለይዞታዎች እና ባለድርሻ አካላት ይገኛሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በትግስት ዘላለም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *