ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ጋር ተወያዩ

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከፊንላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ጋር ተወያይተዋል።

ሁለቱ መሪዎች በውይይታቸውም በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ በቀጠናው በተለይም በሱዳን ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በምታደርገው ጥረት ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጿል።

ፊንላንድ በኢትዮጵያ በተለይም የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎችን በገንዘብና በሰው ሃይል ከሚደግፉ የአውሮፓ አገራት መካከል ዋነኛ ናት።

ኢትዮጵያ ከፊንላንድ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ስዊድን ስቶኮልም በሚገኘው ኢምባሲዋ በኩል የምታቀላጠፍ ሲሆን ፊንላንድ ከ15 ዓመት በፊት ነበር በአዲስ አበባ ኢምባሲዋን የከፈተችው።

ሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነታቸውን ከጀመሩ ከ60 ዓመት በላይ አስቆጥረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *