በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ወጪ የተገነባው የኢትዮጵያ ትምህርትና ጥናት ተቋም ማዕከል ተመረቀ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያ ትምህርትና ጥናት ተቋም በመሆን የሚያገለግል ህንፃ ግንባታው ተጠናቆ በዛሬው ዕለት ከዩኒቨርሲቲው ጋር ርክክብ ተፈጽሟል።

ማዕከሉ 116 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን የግንባታው ሙሉ ወጪም በሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤት ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን የተሸፈነ ነው።

ማዕከሉ ቤተ መጻህፍት፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ቢሮዋች፣ የኤግዚቢሽን ማሳያና የመጻህፍት ክምችት ክፍልና ሌሎች በርካታ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ክፍሎችን እንዲይዝ ተደርጎ እንደተገነባ በምርቀው ወቅት ተገልጿል።

ዘገባው የአባቱ መረቀ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *