በ2011 በጀት ዓመት 198 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ

ባለፉት 12 ወራት 198 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር አስታውቋል።

ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ሚኒስቴሩ በ2011 በጀት አመት 213 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 198 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡

የተሰበሰበው ገቢ ከ2010 በጀት ዓመት አንፃር ሲታይ የ22 ቢሊየን ብር ብልጫ ወይም የ12 በመቶ እድገት አሳይቷል።

ከተሰበሰበውን ገቢ ውስጥ የሀገር ውስጥ ገቢ ድርሻ 120 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ሲሆን 77 ነጥብ 7 ቢሊየን ብሩ ደግሞ ከቀረጥ የተሰበሰበው ነው።

ሚኒስቴሩ በ2012 በጀት ዓመት ደግሞ 248 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ማቀዳቸውን ወይዘሮ አዳነች ገልጸዋል።

ዘገባው የሔኖክ አስራት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *