የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ እስከሚካሂድ ድረስ ከተማዋን ማስተደደሬን እቀጥላለሁ አለ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1995 ዓ.ም የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 361/1995 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር በ2010 ዓ.ም ማሻሻሉ ይታወሳል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስልጣን ዘመን በ2010 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ቢሆኑም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሻሻለዉ አዋጅ መሰረት አስተዳደሩ ዛሬም ከተመዋን እያስተዳደረ ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ ከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን እንዲያስተዳድር የተፈቀደለት የጊዜ ገደብ በመጠናቀቀቁ አዲስ ምርጫ መካሄድ አለበት የሚል ሃሳብ በተደጋጋሚ በመነሳት ላይ ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤምም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስልጣን ዘመን መቼ ይጠናቀቃል? ሲል ምክር ቤቱን ጠይቋል፡፡

የምክር ቤቱ የፕረስና የህዝብ ግንኙነነት ዳይሬክተር አቶ አዲሳለም እንቻለዉ ፤እንደነገሩን የከተማ አስታደሩ ህጋዊነት በሰኔ ሠላሳ 2011 ዓ.ም ተጠናቋል የሚባለዉ ሀሰት ነዉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለምርጫዉ የጊዜ ገደብ አላስቀመጠም ብለዋል፡፡

የአስተዳደሩ የስልጣን ዘመን ከተጠናቀቀ ከ1 አመት በላይ ቢሆነዉም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሻሻለዉ ቻርተር ላይ የጊዜ ገደብ ባለማስቀመጡ ፤ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ አስተዳደሩ ከተመዋን መምራቱን እንደሚቀጥል አቶ አዲስ አለም ተናግረዋል።

አዲስ አበባ እና ድሬ ደዋ ከተማ ተጠሪነጣቸዉ ለህዝብ ተወካዮች እንደሆነ ይታወቃል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን እንዲያደርግ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጣለት መመሪያ እንደሌለም አቶ አዲስ አለም ተናግረዋል፡፡

እኛም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2010 ዓ.ም ያሸሻለዉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር ለመመልከት ሞክረናል፡፡

በዚህም መሠረት አንቀጽ 15 ንኡስ አንቀፅ 2 ሥር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ጊዜ እንዲራዘም የወሰነ እንደሆነ ምርጫ ተደርጎ በምርጫዉ መሠረት አዲስ አስተዳደር እስኪደራጅ ድረስ በስራ ላይ ያለዉ ምክር ቤት እና አጠቃላይ የከተማ አስተዳደሩ በነበረበት ይቀጥላል ይላል፡፡

በአባቱ መረቀ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *