የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለአቶ ተወልደ ገብረማርያም እና ለሀጂ ሙፍቲ ሼክ ዑመር እድሪስ የክብር ዶክትሬት እንደሚሰጥ አስታወቀ

ዩንቨርሲቲው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለሆኑት ለአቶ ተወልደ ገብረማርያም እና ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ካውንስል ሀላፊ እና የዑለማ ሀላፊ ለሆኑት ሀጂ ሙፍቲ ሼክ ዑመር እድሪስ ቅዳሜ ሐምሌ 6 ቀን 2011 ዓ.ም በሚያካሂደው የምረቃ በዓል ላይ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንዲሰጣቸው መወሰኑን አስታውቋል፡፡

የክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ስነስርዓቱም ቅዳሜ ሐምሌ 6 ቀን 2011 ዓ.ም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምረቃ ስነስርዓት በሚካሄድበት በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *