አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት እጩ ሆኑ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበይ አህመድ የደህንነት አማካሪ ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት እጩ ሆኑ

አቶ ዮሃንስ ቧያለው የአዴፓ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ሲያካሂድ የነበረውን የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በዛሬው እለት አጠናቋል።

ውይይቱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የማዕከላዊ ኮሚቴው አቶ ዮሐንስ ቧያለውን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡን አስታውቋል።

በተመሳሳይ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አገኘው ተሻገርን የአዴፓ ስራ አስፈፃሚነና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች አባል ሆነው ተመርጠዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበይ አህመድ የደህንነት አማካሪ ሆነው በማገልገል ላይ ያሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እጩ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ቀርበዋል።

የርዕሰ መስተዳደር ሹመቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።

አቶ ተመስገን በአማራ ክልልና በፌደራል የተለያዩ ተቋማት በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለዋል።

ለአብነትም የሃገር መከላከያ ሰራዊት መረጃ ዋና መምሪያ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር፣ የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና በሌሎች የሃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *