በአዲስ አበባ ቦሌ ድልድይ ስካይ ላይት ሆቴል አካባቢ የመብራት ፖል ወድቆ በአንድ ሰዉ ላይ የሞተ አደጋ ደርሰ

በቦሌ ክፍለ ከተማ ስካይ ላይት ሆቴል ፊት ለፊት ረፋድ 5 ሰዓት አካባቢ መብራት ፖል ተሰብሮ በስራ ላይ በነበረ የመብራት ሀይል ሰራተኛ ላይ የሞት አደጋ አጋጥሟል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤምም አደጋዉን ለማጣራት ወደ ቦታዉ ያቀና ሲሆን የግለሰቡን አስክሬን ተመልክቷል፡፡

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ባለሙያዉ ሳጅን ምትኩ መንገሻ ለጣቢያችን እንዳስታወቁት፤ በአካባቢዉ የሚገኝ አንድ የመብራት ፖል ለመንቀል በክሬን መኪና እየተሰራ ባለበት ወቅት ፤ፖሉ ከክሬኑ አምልጦ በሰራተኛዉ ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡

የመብራት ፖሉ በሰዉ ሃይል አልነቀል በማለቱ በመኪና ክሬን ፖሉን ለማንሳት በሚደረግበት ወቅት ፖሉ በሰረተኛዉ ላይ ማረፉንም ሳጅን ምትኩ ነግረዉናል፡፡

ግለሰቡ ወዲያዉኑ ህይዎቱ ያለፈ ሲሆን የግለሰቡን ማንነት ለመለየት ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ እያደረገ ነዉ ብለዋል፡፡

የመኪናዉ አሽከርካሪም በቁጥጥር ስር መዋሉን ሳጅን ምትኩ ለጣቢችን አረጋግጠዋል፡፡

ዘገባው የአባቱ መረቀ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *