ብሔራዊ ሎቶሪ በ2011 በጀት አመት 192 ሚሊዮን ብር የተጣራ ተርፍ አገኘ

ብሔራዊ ሎቶሪ በአመቱ አገኘዋለሁ ብሎ ያቀደው 171 ሚሊየን ብር ቢሆንም ከእቅዱ በላይ የ12 በመቶ ጭማሪ በማሳየት 192 ሚሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱ ተነግሯል፡፡

ይህም ብሔራዊ ሎቶሪ አስተዳደር በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን ትርፍ የስመዘገበበት ዓመት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በ2010 ዓ.ም በጀት አመት 150 ሚሊየን ብር የተጣራ ትርፍ ያስመዘገበው ብሔራዊ ሎቶሪ አሁን በ39.9 ሚሊየን ብር ብልጫ አስመዝግቧል፡፡

በበጀት ዓመቱ ለተመዘገበው ከፍተኛ ትርፍ የወረቀት ሎቶሪ ሽያጭ መጨመርና ተዛማች ጉዳዮች ላይ ተገቢውን ገቢ መሰብሰብ መቻሉ መሆኑን ሰምተናል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወኑ እጣ ነክ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር ከዘርፉ 15 በመቶ ገቢ የሚያገኝ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከፋብሪካዎችና ከባንኮች በኩል ለተጠቃሚዎች ከሚደርሱ ሽልማቶች የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 15 በመቶ የሚሆነውን መሰብሰቡ ተነግሯል፡፡

ብሔራዊ ሎቶሪ አስተዳደሩ ከጠቅላላ ገቢው 41 በመቶ የሚሆነውን መልሶ ለሎተሪ ባለእድለኞች ለሽልማት የሚያውለው ሲሆን ከጠቅላላ ገቢው 21 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ወደ መንግስት ካዝና ፈሰስ ያደርጋል።

ዘገባው የደረሰ አማረ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *