በደቡብ ክልል የኤች አይ ቪ አድስ ስርጭርትን መቀነስ አልተቻለም

የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ መጠን ከሚታይባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች አንዱ የሆነው የደቡብ ክልል የቫይረሱ ስርጭት መጠን ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎችን ቢሰራም የስርጭት መጠኑን መቀነስ እንዳልተቻለ የክልሉ ጤና ቢሮ ይናገራል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ፕሮግራም ዳሬክተር አቶ ፍስሃ ላላንጎ ለጣቢያችን እንዳሉት በክልሉ የነበረው የሰላም መደፍረስ የቫይረሱ ስርጭት በተወሰኑ ቦታዎች ላይ እንዲያንሰራራ ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት፡፡

በቅርቡ በተሰራ ጥናትም የስርጭት መጠኑ 0.4 ወይም ከመቶ ሰዎች ውስጥ አራቱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ ወስጥ የወንዶች የስርጭት መጠን 0.57 በመቶ፤ የሴቶች 0.25 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን አቶ ፍስሐ ነግረውናል፡፡

ምንም አንኳን የክልሉ ኤች አይ ቪ አድስ የስርጭት መጠን 0.4 በመቶ ቢሆንም በክልሉ በሚገኙ እንደነ ቤንች ማጂ በመሳሰሉ ዞኖች ላይ የስርጭት መጠኑ ወደ 1.9 በመቶ ከፍ ማለቱ ተነግሯል፡፡

የክልሉ ርእሰ መዲና በሆነችው ሃዋሳን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ አካበቢዎች ታላላቅ ፕሮጀክቶች በሚካሄድባቸው ፋብሪካዎችና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የበሽታው ተጋላጭነት እየሰፋ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት ከአንድ በመቶ በላይ ከሆነ በአንድ ሃገር ውስጥ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ወረርሸን ተከስቷል ይባላል።

የውልሰው ገዝሙ እንደዘገበችው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *