ዕለታዊ የስፖርት ዜናዎች

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች የክፍያ መጠን ላይ ያተኮረ ስብሰባ ሊካሄድ ነው፡፡

የስፖርት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ እግርካስ ፌደሬሽን ጋር በመተባበር በተጫዋቾች ዝውውር እና የክፍያ መጠን ላይ ያተኮረ ስብሰባ የፊታችን ነሀሴ 3 ቀን እንደሚካሄድ ነው ያገኝነው መረጃ የሚጠቁመው፡፡

በስብሰባው ላይ የክልል ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽኖች እና የእግር ካስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንቶች የኢትዮጵያ እግርካስ ፌደሬሽን የስራ አስፈጻሚ አባላት 16ቱ የፕሪሚየርሊግ ክለቦችና አዲስ አዳጊ 3ቱ ክለቦች ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ዳኞችና ኮሚሽነሮች የአሰልጣኞች ማህበር ተወካዮች በስብሰባው ላይ እንዲገኙ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡

የአሰልጣኝና የጠጫዋች ዝውውር በከፍተኛ ሁኔታ እየተካሄደ በሚገኝበት በዚህ ሰአት ስብሰባው ዘግይቶ መጠራቱ በቀጣይ ምን አይነት ለውጥ ይፈጠራል የሚለው ተጠባቂ መሆኑ እንዳለ ሆኖ የጉዳዩ ባለቤት የሆኖት ተጫዋቾች ተወካዮች አለመካተታቸው ጥያቄ አስነስታል፡፡

ኢትዮጵያ የተካተተችበት ከ15 አመት በታች የሴካፋ ውድድር ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡

በሴካፋ ታሪክ የመጀመርያ የሆነው ከ15 አመት በታች የወንዶች ውድድር በአስመራ ሲካሄድ የምድብ ድልድልም ወጥቷል፡፡

የክፍለ አሁጉሩ ሀገራት የሚሳተፉበት ይህ ውድድር ከነሀሴ 9 እስከ ነሃሴ 26 በኤርትራ ደሚና አሰመራ ይካሄዳል፡፡

በሶስት ምድቦች 11 ሀገራት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

ኢትዮጵያም በምድብ ለ ከዩጋንዳ ሩዋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ጋር ተደልድላለች፡፡

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው መከላከያን ለማሰልጠን ተሰምቷል፡፡

የቀድሞው ሲዳማ ቡና ደቡብ ፖሊስ ድሬዳዋ ከነማ፡ ወልዲያ ከነማ እና ሌሎችም በርካታ የሀገራችን ክለቦችን በአሰልጣኝነት የመሩት አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ክለቡን ለአንድ አመት ለማሰልጠን መስማማታቸው ታውቋል፡፡

በተያያዘ መረጃ፡ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ባህር ዳር ከነማን ለአንድ አመት ለማሰልጠን በትላንትናው እለት መስማማታቸው የተረጋገጠ ሲሆን፡ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌም በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለተጨማሪ አንድ አመት በክለቡ ለመቀጠል ኮንትራታቸውን ማደሳቸውም ይታወቃል፡፡

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ባህር ዳር ከነማን ለማሰልጠን ተስማማ፡፡

የጣና ሞገዱን ከከፍተኛ ሊግ አሳድገው ለአንድ ዓመት ያህል በፕሪምየር ሊጉ ያሰለጠኑት ጳውሎስ ጌታቸው ከክለቡ ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ጥረት ላይ የነበረው ባህር ዳር ፋሲል ተካልኝን በአንድ አመት ውል እንዲያሰለጥን አስፈርሟል።
ፋሲል በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በተጫዋችነት እንዲሁም ለረዥም ጊዜ በምክትል አሰልጣኝነት መምራቱ የሚታወስ ሲሆን ባህር ዳርን ከመመቀላቀሉ በፊት በኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ምክትል በመሆን እያገለገለ ነበር፡፡

በባህር ዳር ከነማ በኩል ውሉን የተዋዋሉት የክለቡ የቦርድ አባል እና የአዲስ አበባ ተወካይ የሆኑት አቶ ጌታዘሩ፤ በአንድ ዓመት ቆይታው በሚያመጣው ውጤት እና በሚያሳየው እንቅስቃሴ ውሉ ሊራዘም የሚችልበት አንቀጽም ተካቷል።

አሰልጣኙ ከክለቡ ጋር በሚቆይበት ጊዜ ሙሉ የስራ ነጻነት ተስጥቶታል። በቀጣይም ወደ ተጫዋች ዝውውር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ወደ ባህር ማዶ ወሬዎች ስናመራ ዲያጎ ፎርላንን በቅድሚያ እናገኛለን፡፡

ዩሯጓያዊው ዲያጎ ፎርላን ከእግር ኳስ ራሱን አግልሏል፡፡

የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ተጫዋች ዲዬጎ ጎዲን ከፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋችነት ቆይታው ማብቃቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ዩሯጓያዊው ታላቅ ተጫዋች ፎርላን 40ኛ ዓመቱ ላይ የሚገኝ ሲሆን የመጨረሻ ጨዋታውን ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ሆንግ ኮንግ ላይ ከኪትቼ ጋር አድርጓል፡፡

አጥቂው ከማ/ዩ እና አት/ማ በተጨማሪ በጣልያኑ ኢንተር ሚላን እና በስፔኑ ቪያሪያል ቢያሳልፍም በአትሌቲ ግን አመርቂ ቆይታ ነበረው፡፡

ፎርላን ከቴሌሙንዶ ጋር ባደረገው ቆይታ ራስን ለማግለል ቀላል አይደለም፤ ይህ ጊዜ እንዲመጣ ፍላጎቱ አልነበረኝም ነበር ነገር ግን መምጣቱ አርግጥ ሆኗል፡፡ እናም እግር ኳስን መጫወት ማቆም እንዳለብኝ ወሰንኩ ብሏል፡፡

ዲዬጎ ፎርላን የፕሮፌሽናል ህይወቱን የጀመረው በአርጀንቲናው ኢንዲፔንደንቴ ሲሆን 2002 ጥር ላይ ወደ አንግሊዙ ማንችስተር ዩናይትድ አምርቷል፡፡

ከቀያይ ሰይጣኖቹ ጋር በነበረው ቆይታ በ2002- 03 የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን፤ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ የኤፍ ኤ ዋንጫን አሳክቷል፡፡

በ2004 ላይ ደግሞ ወደ ቢጫ ሰርጓጆቹ ቪያሪያል አቅንቷል፡፡

ፎርላን በላ ሊጋው ቆይታ ለቪያሪያል እና አትሌቲኮ ማድሪድ በድምር 240 የሊግ ጨዋታዎችን አድርጎ 128 ጎሎችን አስቆጥሯል፡፡ እንዲሁም የ2009-10 የዩሮፓ ሊግ ድልን አሳክቷል፡፡

በዩሯጓይ ታሪክ ከትልቅ ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ፎርላን አንዱ ሲሆን ለሀገሩ 112 ጨዋታዎችን አድርጎ 36 ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል፡፡

የ2011 ኮፓ አሜሪካን ዋንጫን ያሳካ ሲሆን በ2010 የዓለም ዋንጫ ዩሯጓይ አራተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ የወርቃማ ኳስ ሽልማት ወስዷል፡፡

የኢንተር ሚላን እና ማውሮ ኢካርዲ ውዝግብ አሁንም ቀጥሏል።

የጣልያኑ ኢንተር ሚላን ተጫዋቹን ማውሮ ኢካርዲ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት እንደማይጠቀምበት እና የዝውውር ገበያው ከመዘጋቱ በፊት አዲስ ክለብ እንዲፈልግ ነግሮታል ሲል ላ ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት አስነብቧል፡፡

አንቶኒዮ ኮንቴ ወደ ክለቡ ከመጡ በኋላ ቡድኑን እንደ አዲስ እያደራጁ ሲሆን 3 – 5 – 2 አሰላለፍን ለመጠቀም ውጥን አላቸው፡፡

ለዚህም ያግዛቸው ዘንድ የሮማውን ኢዲን ዤኮ እና የማንችስተር ዩናይትዱን ሮሜሉ ሉካኩ የማስፈረም ፍላጎት አላቸው፡፡

የሮሜሉ ሉካኩ ዝውውር ኢንተሮች በሚፈልጉት መንገድ አለመሄዱን ተከትሎ ኢካርዲን በሚቀጥለው ዓመት ሊጠቀሙበት እንደሚችል ቢነገርም አርጀንቲናዊው ተጫዋች ከጁሴፔ ሚያዛ እንዲለቅ ፍላጉቱ እንዳላቸው ተገልጧል፡፡

የጀርመኑ ክለብ ባየርን ሙኒክ የአያክ አምስተርዳሙን ኮከብ ሃኪም ዚዬች የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተዘግባል፡፡

የ26 ዓመቱ ሞሮኳዊ ተጫዋች ስሙ ከአርሰናል ጋር ቢያያዝም አርሴናል ግን ኒኮለላስ ፔፔን አስፈርማል ስለሆነም ባየርሙኒክ ተጫዋቹ ሊያገኝው ይችላል እየተባለ ነው፡፡

አያክስ ባለፈው የውድድር ዓመት አስገራሚ ጉዞ ሲያደርግ 49 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 21 ጎሎችን ሲያስቆጥር 24 ጎል የሆኑ ኳሶችን ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል ይህ ተጫዋች፡፡

ቀያይ ሰይጣኖቹ በክረምቱ ትኩረት አድርገውበት የነበረው የስፖርቲንግ ሊዝበኑ ፖርቱጋላዊ አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በሌሎች ክለቦች ኢላማ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ፤ ትኩረቱን ወደ ኤሪክሰን አድርጓል፡፡

የ24 ዓመቱን ዴንማርካዊ ክሪስቲያን ኤሪክሰንን ዩናይትድ ለማስፈረም መቁረጡንም እስካይ ሰፖርት አስነብቧል፡፡

ቶተንሃም የፕሪምየር ሊጉ የዝውውር መስኮት በመጪው ሐሙስ ምሽት ከመዘጋቱ አስቀድሞ ከአውሮፓ ክለቦች ለተጫዋቹ የሚመጡትን ጥያቄ ላለመግታት እና ለመቀበል የራሱን ጥረት እያደረገ መሆኑን እና ከ50 ሚሊዬን ፓውንድም በታች ቢሆን ቢያገኝ አይኑን አያሽም እተባለ ነው፡፡

ስፐርሶች ከሀሙስ በፊት ቢያንስ ከብሩኖ ፈረንናዴዝ እና ጆቫኒ ሎ ሴልሶ እንዳቸውን ነጩን ማሊያ ማልበስ እንደሚፈልጉ ነው የተነገረው፡፡

ዘገባው የሔኖክ ወ/ገብርኤል ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *