ከሀረር ወደ ኢዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ልዩ ስሙ ቦርደዴ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

8 Aug by Ethio

ከሀረር ወደ ኢዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ልዩ ስሙ ቦርደዴ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

በአካባቢው በተፈጠረ ግጭት መንገዱ በመዘጋቱ ምክንያት ምንም ዓይነት መኪና እንዳያልፍ ተዘግቷል፡፡

ከሀረር ወደ አዲስ አበባ ፣አዳማ እንዲሁም ሌሎች አካቢዎች ለመሄድ የተሳፈሩ ተጓዦች ከማለዳው 2 ሰዓት ጀምሮ መንገዱ መዘጋቱን እና በረሀ ላይ መሆናቸውን መንቀሳቀስም እንዳልቻሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ጥቆማውን የሰጡን ግለሰቦች እንዳሉን ከቦርደዴ – አዋሽ መግቢያ ድረስ መኪኖች መንቀሳቀስ ባለመቻለቸው ተሰልፈው መቆማቸውን እና ይህ ነው ብሎ የተፈጠረውን ችግር ያስረዳቸውም ሆነ መፍትሄ የነገራቸው አካል እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡

መንገዱ የተዘጋውም በግጭት ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ ወደ አሰብ አስክሬን ጭኖ የሚያልፍ መኪና ማየታቸውንም አክለዋል፡፡

የሚመለከተው አካል ጉዳዩን አጣርቶ መፍትሄ እንዲሰጣቸውና የተፈጠረውን ችግር እንዲያስረዳቸውም ጠይቀዋል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎችም ቢሆኑ ግጭት መፈጠሩን ያረጋገጡልን ሲሆን ተፈጠረ ባሉት ግጭትም 7 ሰዎች ሞተዋል፤ 3 ሰዎች ደግሞ በህይወት እና በሞት መካከል ናቸው ብለዉናል፡፡

ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩን ፖሊስ ገና እያጣራሁ ነዉ ያለን ሲሆን ዝርዝር መረጃዉ እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

ትዕግስት ዘላለም እንደዘገበችዉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *