ኢትዮጵያ በ2011 በጀት ዓመት ከውጪ ሃገራት ጎብኝዎች ያገኘችው ገቢ የእቅዷን 55 በመቶ ብቻ ነው ተባለ

9 Aug by Ethio

ኢትዮጵያ በ2011 በጀት ዓመት ከውጪ ሃገራት ጎብኝዎች ያገኘችው ገቢ የእቅዷን 55 በመቶ ብቻ ነው ተባለ

ሃገሪቷ በበጀት አመቱ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የውጭ አገራት ጎብኚዎችን በመሳብ 5.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳ ነበር።

ይሁንና በተጠቀሰው ዓመት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ጎብኚዎች ቁጥር 849 ሺህ 122 ሲሆኑ የተገኘው ገቢም 3.1 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ነው፡፡

የዘንድሮው አፈጻጸም በ2010 በጀት ዓመት ከተገኘው 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ ማሳየቱ ተገልጿል።

በተመሳሳይም ከሃገር ውስጥ ጎብኚዎች ለማግኘት ከታቀደው ገቢ 64 በመቶ ነው ማሳካት የተቻለው፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ታሪኩ ነጋሽ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት ለእቅዱ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን ፤በሃገሪቷ ተለያዩ አካባቢዎች የነበሩ የጸጥታ ችግሮች ትልቁ ምክንያትነት ነው ብለዋል።

በተጨማሪም በቱሪዝም ዘርፍ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት አገልግሎት ሰጪ ተቋሞቻችን ዘመናዊ ቴክኒሎጂ መጠቀም ይገባቸዋል ብለውናል፡፡

በቀጣይም የቱሪዝም ልየታና ትንተና በማድረግ የመዳረሻ አካባቢዎችን ለማልማት እንደሚሰሩ ነግረውናል፡፡

የጎብኚዎችን ቁጥር ሊጨምሩ የሚችሉ አለም አቀፋዊ የንግድ ትርኢቶችን ማካሄድ ማቀዳቸውንም ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በ2012 በጀት አመትም ከውጪ ጎብኚዎች 5.1 ቢሊዮን ዶላር የማግኘት እቅድ እንዳለው ነው አቶ ታሪኩ ለጣቢያችን የተናገሩት፡፡

ዘገባው አባይነሽ ሽባባው ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *