የላይቤሪያ ሆስፒታል ጠያቂ ያጡ ሟቾችን ሊቀብር ነው

በሃገሪቷ ትልቁ ሆስፒታል የሆነው ጆን ኤ ኬኔዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ዛሬ 15 ሟቶችን ለመቅበር ተዘጋጅቷል፡፡

የሆስፒታሉ ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር ጄሪ ብራውን ትናንት በሃገሪቷ ብሄራዊ ሬዲዬ እንደተናገሩት ሟቾቹ ከመጋቢት እስከ ሰኔ ወር ባለው ጊዜ ውስጥ በሆስፒታሉ ህይወታቸው ያለፈ ቢሆንም እስካሁን ጠያቂ ቤተሰብ አልተገኘም፡፡

መቃብራቸውም በጅምላ ሊሆን እንደሚችል ነው አስተዳዳሪው የተናገሩት፡፡

ከሰኔ መጨረሻ እስከ ነሃሴ ድረስ ያሉ ሟቾች ግን በዚህ የጅምላ ቀብር እንደማይካተቱ አስታውቀዋል፡፡ ለቤተሰቦቻቸው ለማስረከብ በቂ ጊዜ እንዳላቸው በመግለጽ፡፡

እንደ ቢቢሰሲ ዘገባ የላይቤሪያ ኢኮኖሚያዊ ድቀት የዜጎችን ሂወት ከባድ ያደረገው ሲሆን የቀብር ወጪም ከብዙዎቹ አቅም በላይ ነው፡፡

ኢኮኖሚያዊ ችግሩ በጤናው ዘርፍ አስፈላጊ ግብአቶችን ለማሟላት ስላላስቻላቸው ለመድሃኒት አቅርቦት የሃገር ውስጥ ሻጮችን እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል፡፡

ጆን ኤፍ ኬኔዲ መታሰቢያ ሆስፒታል በፈረንጆቹ 1970 የተከፈተ ሲሆን በወቅቱ በምእራብ አፍሪካ ምርጡ የጤና ማእከል ነበር፡፡

በአባይነሽ ሽባባው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *