የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ከደረጃ ሐ ግብር ከፋዬች 3.8 ቢሊዮን ብር መሰብሰብን ገለጸ

9 Aug by Ethio

የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ከደረጃ ሐ ግብር ከፋዬች 3.8 ቢሊዮን ብር መሰብሰብን ገለጸ

በባለስልጣኑ ታክስ ጉዳዬች ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዬሴፍ ግርማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት ከደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 3.8 ቢሊዬን ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡

በዘንድሮው አመት በርካታ ግብር ከፋዬች በወቅቱ ግብራቸውን በማሳወቅና በመክፈል የሚበረታታ ተግባር ፈጽመዋልም ብለውናል፡፡

በሲስተም ችግር ምክንያትና በግል ምክንያቶች ግብራቸውን ያልከፈሉ ጥቂት ደንበኞች መኖራቸው አይቀርም ያሉን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤እነዚህ ደንበኞች ሲያጠናቅቁ አፈጻጸማችንን ከፍ ያደርገዋል ብለን እንጠብቃለን ብለውናል፡፡

በአባይነሽ ሽባባው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *