የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በሃምሌ ወር 51 ሺህ ቶ ምርት ማገበያየቱን ገለጸ

ምርት ገበያው ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው ሃምሌ ወር ላይ 51 ሺህ ቶን ምርት በ2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ማገበያየቱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

ከተገበያዩት ምርቶች መካከል ቡና 32 ሺህ 291 ቶን፣ አኩሪ አተር 11 ሺህ 273 ቶን እንዲሁም 5 ሺህ 817 ቶን ሰሊጥ በብዛት የተገበያዩ የምርት አይነቶች ናቸው።

የቡና ምርት ግብይት ከሰኔ ወር ጋር ሲነጻጸር በ30 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2011 በጀት አመት 681 ሺህ ሜትሪክ ቶን የግብርና ምርቶችን በ33.7 ቢሊየን ብር አገበያይቻለሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡

ዘገባው የሳሙኤል አባተ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *