ለኢቦላ ቫይረስ መከላከያ እየተሰጡ ካሉ መድኃኒቶች ውስጥ ሁለቱ የማዳን አቅማቸው ወደ 90 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገለጸ

ለኢቦላ ቫይረስ የሚሰጡ መድሀኒቶች ላይ በተደረገ ተከታታይ ሙከራ 2 መድሀኒቶች ላይ ቫይረሱን የመቋቋም መጠናቸው ማደጉን ተመራማሪዎች አደረግነው ባሉት ተከታታይ ምርመራ ለማወቅ ችለዋል፡፡

መድሃኒቶቹ በቅርቡ ቫይረሱን መቆጣጠር እና ማከም የሚቻልበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ ሲሉም ተስፋ ጥለውበታል፡፡

የቫይረሱ ስርጭት እየተፋጠነ ባለባት ዴሞክራቲክ ኮንጎ 4 መድሀኒቶች ለታማሚዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

ከነዚያ ውስጥ REGN-EB3 እና mAb114 የተባሉት ሁለቱ መድሀኒቶች ህመሙን ከማከም አንፃር የተሻለ ውጤት ማሳየታቸውን ነው ተመራማሪዎቹ ያስታወቁት፡፡

የአሜሪካ ብሔራዊ የአለርጂ እና ተላላፊ ህመሞች ተቋም NIAID መድሀኒቶቹ ባለፉት 1 ዓመት በሀገሪቱ ለ1 ሺ 800 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ቫይረስ ለመቆጣጠር ተስፋ ሰጪ ውጤት ማሳየቱን ቢቢሲ ዘገቧል።

በትግስት ዘላለም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *