ዓለማችን በየዕለቱ 3 ሺህ ወጣቶችን እያጣች እንደሆነ የዓለም የጤና ደርጅት ገለጸ

የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳየው ከአጠቃላዩ 7 ነጥብ 2 ቢሊየን የዓለም ህዝብ ቁጥር 3 ቢሊየኑ እድሜአቸው ከ25 ዓመት በታች ናቸው።

ይህ የወጣቶች ቁጥር ከአጠቃላዩ የህዝብ ቁጥር 47 በመቶውን ድርሻ ይይዛል፡፡

1 ነጥብ 2 ቢሊየኑም ከ 10 እስከ 19 የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡

ታዲያ ከነዚህ ወጣች መካከል ነው ዓለም በየቀኑ 3ሺ ወጣቶችን በሞት ትነጠቃለች የተባለው፡፡

እ.አ.አ በ2016 ብቻ በተደረገ ጥናት እንኳን 1 ነጥብ 1 ሚሊየን እድሜአቸው ከ 10 እስከ 19 ያሉ ወጣቶች በአደጋ፣ በወሊድ ወቅት በተፈጠረ አደጋ ፣በኤች አይ ቪ እና በሌሎችም ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጤና ወኪል በበኩሉ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች፣ ጥቃቶች፣ የመኪና አደጋዎች፣ ሲጋራ ፣ አንደንዛዥ እፅ እና የአልኮል መጠጦች በመገናኛ ብዙሀኑም ሆነ በማህበራዊ ድረገፆች ላይ በስፋት መነገር ወጣቶቹን ለአስከፊ ጉዳት ተጋላጭ ከሚያደርጓቸው እና ፈተና ከሆኑባቸው ጉዳዮች ተርታ መድቧቸዋል፡፡

80 በመቶ እድሜያቸው ከ 15 እስከ 19 የሆኑ ወጣቶች ደግሞ በጭንቀት እና በድብርት ምክንያት ራሳቸውን ማጥፋታቸውም በሪፖርቱ ተካቷል፡፡

የዓለምን 47 በመቶ ድርሻ የያዙ እነዚህ ወጣቶች ጤና ላይ የዓለም ጤና ድርጅት በተለየ ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚኖርበት ድርጅቱ ማሳሰቡን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።

በትግስት ዘላለም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *