ቻይና የሆንግ ኮንግ ተቃውሞ ሰልፈኞችን ሽብርተኞች ናቸው አለች

14 Aug by Ethio

ቻይና የሆንግ ኮንግ ተቃውሞ ሰልፈኞችን ሽብርተኞች ናቸው አለች

በሆንግ ኮንግ የሚገኘው የቻይና ቢሮ እንዳለው ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጸረ መንግስት ናቸው ከሽብርተኞች የተለዩ አይደሉም ብሏል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የቻይና ጦር ወደ ሆንግ ኮንግ መጠጋቱን ጠቅሰው ቻይና ጉዳዩን ሰከን ባለ መንገድ እንድትመለከተው ጠይቀዋል ፡፡

መቀመጫውን በቤጂንግ ያደረገው የሆንግ ኮንግ እና ማካኡ ጉዳዮች ቢሮ መረን የለቀቀ ብጥብጥ እና ግጭት በህጉ መሰረት ተገቢውን ቅጣት ሊያገኝ ይገባል ብሏል ፡፡

በጠንካራ ቃላት የተሞላው የቻይና ማዕከላዊ መንግስት መግለጫ የወጣው ጥቁር ለባሾቹ ሰላማዊ ሰልፈኞች ከሆንግ ኮንግ አድማ በታኝ ፖሊሶች ጋር በሆንግ ኮንግ አለማቀፍ አየርማረፊያ ከተጋጩ በኋላ ነው ፡፡

የአየር ማረፊያው ሰራተኞች በደም እና ፍርስራሽ የተሸፈነውን ወለል ሲያጸዱ የተወሰኑ ተቃዋሚ ሰልፈኞች በዚያው እንደነበሩም ታውቋል ፡፡

ለአስር ወራት የዘለቀው በፖሊስ እና ዲሞክራሲያዊ መብታቸው እንዲከበር በሚጠይቁ ሰልፈኞች መካከል የሚደረገው ግጭት የእስያ የፋይናንስ ማዕከል ተደርጋ የምትቆጠረው ሆንግ ኮንግ በ1997 ከእንግሊዝ አገዛዝ ወደ ቻይና ከተዛወረች በኋላ ታይቶ የማይታወቅ አስከፊ ቀውስ ማስከተሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *