ሆንግኮንግን ከቻይና ለመነጠል የሚደረግ ማንኛውንም ሙከራ ቻይና እንደማትታገስ አስታወቀች

9 Sep by EthioFM

ሆንግኮንግን ከቻይና ለመነጠል የሚደረግ ማንኛውንም ሙከራ ቻይና እንደማትታገስ አስታወቀች

ሆንግኮንግ የማትነጠል የቻይና አካል ነች፡፡ ማንኛውም ለመነጠል የሚደረግ ሙከራ አይሳካም፡፡ ሲል ዛሬ ገልጧል የሃገሪቱ የመንግስት ሚዲያ።

ቻይና ዴይሊ የተባለው ጋዜጣም ከእሁዱ በሆንግ ኮንግ ከተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ከመጀመርያውም የውጪ ሃይሎች ከጀርባ እንዳሉ ማረጋገጥ ችለናል ሲል አትቷል፡፡

ትዕይንተ ህዝቡ መቆም እንዳለበት ያሳሰበ ሲሆን የማዕከላዊ መንግስትን ትዕግስትም እየተፈታተነ እንደሆነ ገልጧል፡፡

የቻይና የመንግስት ሃላፊዎችም የውጪ ሃይሎች በሆንግ ኮንግ ሁከት በማስነሳት እየከሰሷቸው ነው፡፡

ሰላማዊ ሰልፎቹ የመብት ወይ ዲሞክራሲ ጥያቄዎች አይደሉም፣ የውጪ ጣልቃ ገብነት ውጤት እንጂ፤ ማንም ሊገዳደረው የማይገባ እውነትና ሊሰመርበት የሚገባ ሃቅ ሆንግ ኮንግ ከቻይና የማትነጠል ዋና አካሏ መሆኗ ነው ብሏል በጋዜጣው የሰፈረው ፅሁፍ፡፡

ሰላማዊ ሰልፈኞቹም፣ የውጩ ሃይሎችም ቆሻሻ ጨዋታቸውን መጫወት ቢቀጥሉም ይሄን መቀየር አይችሉም ብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *