በአቃቂ ገበያ ላይ ዛሬ ሌሊት የተነሳው ድንገተኛ የእሳት አደጋ እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም

9 Sep by EthioFM

በአቃቂ ገበያ ላይ ዛሬ ሌሊት የተነሳው ድንገተኛ የእሳት አደጋ እስካሁን በቁጥጥር ስር አልዋለም

በአደጋው ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት መውደሙ ተገልጿል።

በአቃቂ ገበያ እሁድ ለሰኞ አጥቢያ ላይ የተነሳው ይህ እሳት አደጋን ለመቆጣጠር እየተሞከረ ቢሆንም ቃጠሎው አሁንም በቁጥጥር ስር አልዋለም ተብሏል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አቃቂ ገበያ ትላንት ሌሊቱን በእሳት አደጋ ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰበት በአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

አስካሁን በቁጥጥር ሰር ማዋል ባልተቻለው በዚህ አደጋ በሰው አካል ላይ ጉዳት አልደረሰም።

በአደጋውም 60 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት ቢወድምም 200 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት ማዳን ተችሏል ተብሏል።

የደረሰውን የእሳት አደጋ ለመቆጠጣጠር 15 የአደጋ ተሽከሪካሪዎች ተሰማርተዋል፤ አምስት ቦቲ ተሽከርካሪ፣ አምስት ቀላል ተሽከርካሪ፣ ሁለት አምቡላንስ፣ 552 ሺህ ሊትር ውሃ ፣ ወደ 2 ሺህ ሊትር ፎም እንዲሁም 136 ሰራተኞች እና አመራሮች ርብርብ እያደረጉ ነው ተብሏል።

አደጋውን እስካሁን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል የተለያዩ አካላት እንዲያግዙም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *