ኢትዮጵያ በ2030 በአፍሪካ ቀዳሚ የኢኮኖሚ ባለቤት መሆን የሚያስችላትን እቅድ ይፋ አደረገች

9 Sep by EthioFM

ኢትዮጵያ በ2030 በአፍሪካ ቀዳሚ የኢኮኖሚ ባለቤት መሆን የሚያስችላትን እቅድ ይፋ አደረገች

እቅዱ ባሳለፍነው ሳምንት የተጀመረው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮጀክት አንዱ አካል ነው ተብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ኢትዮጵያ በ2030 የአፍሪካ ብልጽግና ምልክት እንድትሆን የሚያስችላትን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ይፋ አድርገዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከልማት አጋሮችና ከዲፕሎማሲያዊ ማኅበረሰብ ጋር በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ ዛሬ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በመድረኩም በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ገጽታውን ለመለወጥ የተከናወኑትን ቁልፍ ክንውኖችን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ይህንን ለማሳካት የልማት አጋሮች ድጋ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *