በ2011 በጀት ዓመት በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች የ1 ሺህ 229 ሰዎች ህይወት አልፏል

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንዳስታወቀው በ2011 በጀት ዓመት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ የ1 ሺህ 229 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤በ1 ሺህ 393 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ሲደርስ በ19 ሰዎች ላይም የግድያ ሙከራ ተፈጽሞባቸዋል።

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት በተጠቀሰው ዓመት በተፈጠሩ ግጭቶች ላይ በተሳተፉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡

በነዚሁ ግጭቶች ሳቢያም ከሁለት ቢሊየን በላይ ብር የሚገመት የዜጎች ንብረት የወደመ ሲሆን፤1 ነጥብ 2 ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸውና ከአካባቢያቸው ተፈናቅለዋል።

በዚህ ግጭት የተሳተፉ 1 ሺህ 323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቶ ከእነዚህ መካከል 645 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየታየ ሲሆን 667 ተጠርጣሪዎች እንዳልተያዙ ተገልጿል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል በጃዊ ወረዳና በመተክል ዞን ፤በጎንደርና አካባቢው በተፈጠረ ሁከትና ብጥብጥ፤በሰሜን ሸዋ አስተዳደር እንዲሁም በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል ከማሻ ዞን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎችና የዚሁ ዞን አጎራባች በሆነው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞን በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ በተፈፀመ ብጥብጥና ሁከት በአሶሳ ዞን አራት ወረዳዎች ውስጥ በኦሮሚያና በበርታ ብሄረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት ተሳታፊ ከነበሩ 1 ሺህ 647 ተጠርጣሪዎች ውስጥ 185 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

መረጃው የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *