የፊፋ የዓለም ምርጡ ተጫዋች

አርጀንቲናዊው ትላንት ምሽት በተከናወነ ስነስርዓት ለስድስተኛ ጊዜ የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል ፡፡

ባርሴሎና በ2018/19 የውድድር ዘመን ካስቆጠራቸው 90 ጎሎች 55 በመቶ ያህሉ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል ፡፡ አስቆጥሯል አሊያም አመቻችቶ አቀብሏል ፡፡

የዓምና ስኬቶቹ :
የላ ሊጋ ዋንጫን አሸንፏል ፡፡ ቡድኑ በቻምፒየንስ ሊግ እና ኮፓ ዴል ሬይ ግማሽ ፍጻሜ እንዲደርስ ረድቷል ፡፡

የአውሮፓን የወርቅ ጫማን አሸንፏል ፡፡ የአውሮፓ ከፍተኛው ጎል አስቆጣሪ እና በላ ሊጋው ቀዳሚው ጎል የሆኑ ኳሶች አቀባይ ነበር ፡፡

በ2019ኙ ኮፓ አሜሪካ አርጀንቲና የነሃስ ሜዳሊያ እንድታገኝ ረድቷል ፡፡
የስፔን እግር ኳስ ጸሃፊ አንዲ ዌስት ስለ እርሱ እንዲህ ይላል …
ሊዮኔል ሜሲ የዓለም ምርጡ ተጫዋች መሆኑን ለማወቅ አንድ መሟላት የሚገባው ቅድመ ሁኔታ አለ ፡፡ እግር ኳስን የሚያዩ ዓይኖች ባለቤት መሆንን ይጠይቃል ፡፡

በትክክል ለተመለከተው እርሱ ከሌሎቹ እጅግ እንደሚልቅ ለመረዳት ጊዜ አይፈጅበትም ፡፡ በእርሱ እና በቅርብ ተፎካካሪዎቹ መካከል ያለው የክህሎት ልዩነት እጅግ የሰፋ ነው ፡፡

እርሱን ስትመለከቱ ጎሎችን ታያላችሁ ፡፡ ኳስን ገፍቶ ሲሄድ (dribbles) መመልከትም ብርቅ አይሆንም ፡፡ ለማመን የሚከብዱ ተከላካይ ሰንጣቂ ፓሶችን ያደርጋል ፡፡ ሜዳውን 360 ዲግሪ ይመለከታል ፡፡ በዙሪያው ምን እንደሚከናወን በሚገባ ያውቃል ፡፡ በርካታ ተጫዋቾች እርሱን ለማቆም እየጣሩ አልፏቸው ይሄዳል ፡፡ ጨዋታውን የሚያከናውነው ከራስ ወዳድነት ፍጹም በጸዳ መንገድ ነው ፡፡ እነዚህን ሁሉ ከተመለከታችሁ በኋላ ያለማንም አስገዳጅነት እውነት ነው እርሱ የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች ነው ብለው ይመሰክራሉ ፡፡ ያውም በሰፊ ርቀት ፡፡

ዓይኖት እዚህ መደምደሚያ ላይ ሊያደርሶት ካልቻለ ግድየለም ቁጥሮችን ይመልከቱ፡፡ ያን ጊዜ ሁሉ ነገር ቀለል ይልሎታል ፡፡ በ2018/19 በመላው አውሮፓ የእርሱን ያህል በርካታ ጎሎችን ያስቆጠረ የለም ፡፡ 36በላ ሊጋ በድምሩ በሁሉም ውድድሮች 55 ፡፡ ከእርሱ የሚከተለው 33 ጎሎች ያሉት ኪልያን ምባፔ ነው፡፡
ሌሎች መለኪያዎችንም እንመልከት …ጎል የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ከአውሮፓ (አምስተኛ ) ነበር ፡፡ በክፍት ጨዋታ ዕድሎችን በፍጠር አሁንም ከአውሮፓ (ሶስተኛ )ነበር ፡፡ ድሪብሎችን በማድረግ (አራተኛ)…ወደማጥቃት ቀጠናው final third ፓስ በማድረግ (ሁለተኛ) and በርካታ ሙከራዎች በጎሉ ብረት የተመለሰበት ቀዳሚው ተጫዋችም ነበር ፡፡ አጥቂ. ፕሌይሜከር እና የመስመር ተጫዋች ነው ፡፡ ሁሉንም በአንድ የሚከውን ፡፡

ዋንጫዎችን ለክለቦች የሚያመጡት እንደዚህ ያሉ የግለሰቦች ውጤታማነት ናቸው ፡፡ ባርሴሎና ከአትሌቲኮ ማድሪድ በ11 ነጥቦች በልጦ ላ ሊጋውን እንዲያሸነፍ የአንበሳውን ድርሻ የተጫወተው ደግሞ ሜሲ ነበር ፡፡
በቻምፒየንስ ሊግም ቢሆን ልቀቱን አሳይቷል ፡፡ በ12 ጎሎች የውድድሩ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ጨርሷል ፡፡

በአንፊልድ በሊቨርፑል በተሸነፉበት ጨዋታ እንኳን ሳይቀር በርካታ ዕድሎችን በመፍጠር እና ዒላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን በማድረግ ቀዳሚው እርሱ ነበር ፡፡ የሊቨርፑል ተጫዋቾች እንኳን አይደርሱበትም ፡፡
የቡድን ጓደኞቹ እንዴት የፈጠሯቸውን ዕድሎች መጨረስ እንዳለባቸው እና እንዴት መከላከል እንዳለባቸው ከዘነጉ እርሱ ተጠያቂ የሚሆንበት ምንም ምክንት አይኖርም ፡፡

የሜሲ ችግር ግልጽ ነው ፡፡ እርሱ ማድረግ የማይችለው ነገር የለም ተብሎ ተደምድሟል ፡፡ ባለፈው ጥቅምት ዌምብሌይ ላይ ቶተንሃምን እንዳልነበር ሲያደርግ ሁሉም ሰው አልተደነቀም ፡፤ ሜሲ እኮ ነው ብሎ አለፈው ፡፡ በአንድ አጋጣሚ እንኳን ቢሆን ያንን ያደረገው ሌላ ተጫዋች ቢሆን ተዓምር ተሰራ እንላለን ፡፡ ሜሲ ሲሆን ግን እንደ ተራ ነገር እቆጥረዋለን ፡፡ ምክንቱም ተለማምደነዋል ፡፡

ይህ ሁሉ ካላሳመኖት ግን ከመጨረሻዎቹ ዕጩዎች አንዱ ሆኖ የቀረበው ቫን ዳይክ የሰጠውን ምስክርነት ያድምጡ ፡፡ ባርሴሎናን በተቃራኒ ከገጠሙበት ጨዋታ በኋለካ ‹‹ ሜሲ አሁንም ድረስ የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች ነው ፡፡ እግር ኳስን መጫወት እስካላቆመ ድረስ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ መመረጥ ያለበት እርሱ ነው ›› ብሎ ነበር ፡፡ ሆላንዳዊው አልተሳሳተም ፡፡ አርጀንቲናዊው ዳግም ወደ ዙፋኑ ወጥቷል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *