ኩዱ ቬንቸር የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ስራ ፈጣሪ እንስቶችን ለማበረታታት 30 ሚሊዮን ብር መመደቡን ገለጸ

ኩዱ ቬንቸር የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሴት ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ነው የ30 ሚሊየን ብር የኢንበስትመንት ድጋፍ ማድረጉን ያስታወቀው።

አይ ኩድ ላይፍስ ከተሰኘው መሰል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ለመስራትም ስምምነት ላይ መድሱንም ትናንት በስጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል።

የ ኩድ ቬንቸር ዳይሬክተር አቶ ኖኤል ዳንኤል በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት ድርጅቱ በምስራቅ አፍሪካ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ስራዎች ላይ ተሣትፎ ማድረጉንና በተለይም ሴት ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ይህንን የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።

የአይ ኩድ ላፍስ ዳይሬክተር የሆኑት ቤተልሄም ደሴ በበኩላቸው ይህ የኢንቨስትመንት ገንዘብ ድጋፍ በዋናነት ትኩረቱን በሴቶች ላይ ያድርግ እንጂ የጾታ፣የእድሜ ገደብ ሣይኖረው ማኛውንም ስራ ፈጣሪ የተሻለ ሃሳብ ይዞ መምጣት የሚችል ሁሉ ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል በይበልጥ ግን ለሴቶች ቅድሚያ ይሰጣል ነው የተባለው።

ይህንን ድጋፍ ለማግኘት የተቀመጠ መስፈርት አለ ወይ የገንዘብ ድጋፍ መሰጠት የሚጀምረውስ መቼ ነው ተብሎ ከጋዜጠኞች ለተነሣው ጥያቄ ድጋፉን ለማግኘት የተሻለ የፈጠራ ሃሣብ ብቻ እንደሚያስፈልግ ነግረውናል።

ድጋፍ የሚጀመርበት ጊዜ በተመለከተ ወደፊት በድርጅቶቹ ዌብ ሳይትና በተለያዩ መተግበሪያዎች ይፋ ይሄናሉ ተብላል።

የውልሰው ገዝሙ እንደዘገበችው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *