የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን አስመለክቶ ከ48 ቀናት በኋላ ለሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክቶች ይፋ ሆኑ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን በማስመልከት ለማካሄድ ላቀደው ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።

በዚህ በፊት ቦርዱ ይፋ ባረገው የድርጊት መርሀ ግብር ላይ ቦርዱ ሁለቱ የህዝበ ውሳኔው አማራጭ ሃሳቦች የሚወከሉበትን አማራጭ ምልክቶች ይፋ እንደሚያደርግ በገለጸው መሰረት ይህንኑ አስመልክቶ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት እና ከሲዳማ ዞን ምክር ቤት ጋር ምክክር ያደረገ ሲሆን

በዚሁ መሰረት፡-
1. “ሲዳማ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ውስጥ እንዲቆይ እፈልጋለሁ” ለሚለው አማራጭ የጎጆ ቤት ምልክት፣

2. “ሲዳማ ራሱን ችሎ በክልልነት እንዲደራጅ እፈልጋለሁ” ለሚለው አማራጭ የሻፌታ ምልክት ሆኖ ለህዝበ ውሳኔው ድምጽ መስጫነት እንዲያገለግል መወሰኑን ቦርዱ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

በሳሙኤል አባተ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *