ዩናይትድ ላይ ጎል ያስቆጠረው ታዳጊ ጠዋት ፈተና ተቀመጠ

ሉክ ማቲሰን 16 ዓመቱ ነው ፡፡ የGCSE ፈተናውን የወሰደው ከወር በፊት ነው ፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን ለሮችዴል በሰባት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል ፡፡

ትላንት ምሽት በካራባኦ ዋንጫ ሮችዴል በኦልድ ትራፎርድ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ሲጫወት ሉክ ማቲሰን ጎል አስቆጥሯል ፡፡

ታዳጊው ፈጽሞ የማይረሳው አጋጣሚ ነበር ፡፡ ነገር ግን ደስታውን ረዘም ላለ ጊዜ ማጣጣም አልቻለም ፡፡ ዛሬ ጠዋታ ወደ ትምህርት ቤት መመለስ ነበረበት ፡፡

‹‹ ኳሷን መረብ ላይ ካሳረፍኳት በኋላ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ስሜት ተሰማኝ ›› ይላል ማቲሰን ፡፡

‹‹ወደ ሮችዴል ደጋፊዎች አቅጣጫ ሮጥኩ ፡፡ በጉልበቴ ፊት ለፊታቸው ተንሸራተትኩ ፡፡ ልዩ ቅጽበት ነበር ፡፡

‹‹በዚያ ጨዋታ ላይ የተገኘሁት ከትምህርት ቤት ቀርቼ ነው ፡፡ ያንን በእረፍት ቀኔ አካክሰዋለሁ ፡፡ ጠዋት ላይ ግን የ psycology ፈተና ስላለኝ ወደ ትምህርት ቤት እሄዳለሁ ›› ብሏል ማቲሰን ከጨዋታው በኋላበሰጠው አስተያየት፡፡

‹‹ እግር ኳስ ዋስትና ሊሆን አይችልም ፡፡ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም ፡፡ የዓለም ምርጡ ተጫዋች ልትሆን ትችላለህ …በተቃራኒው ሊሆን የሚችልበት ዕድል እንዳለም ከግምት ማስገባት ጥሩ ነው ፡፡ ስለሆነም ትምህርትን ጠበቅ ማድረግ መልካም ነው›› በሚል አስተያየቱን ቋጭቷል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *