በዓባይ ወንዝ ዙሪያ ከትብብር ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ

ኢትዮጵያን ወክለው በ74 ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ በዚህ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግራቸው የአባይ ወንዝ ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ሃብት እንጂ የጥርጣሬ እና የውድድር ምንጭ ሊሆን አይገባም ብለዋል።

ከ100 ሚሊዮን ላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ ከ64 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች መብራት እንደማያገኙ ገልጸው የመንግስት የመጀመሪያው እቅድ ኢትዮጵያዊያን እራታቸውን በመብራት እንዲበሉ ማስቻል ነው ሲሉ የአባይን ወንዝ መጠቀም የግድ እንደሆነ ገልጸዋል።

የአባይን ወንዝ የጋራ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ለመጠቀምም የተፋሰሱ ሀገራት በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

አፍሪካ በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ አንዲኖራትም ጠይቀዋል ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ።

የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ከሁለት ቀናት በፊት በዚሁ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የግብጽን ጥቅም እንደሚጎዳና ለቀጠናው አገራት አለመረጋጋት ምክንያት ሊሆን ይችላል ማለታቸው አይዘነጋም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *