ሰባስታያን ኩርዝ የሚመራው የኦስትሪያ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ትላንት የተካሂደውን የምክር ቤት ምርጫ በአብላጫ ድምፅ አሸነፈ

ወግ አጥባቂዉ የሰበስታያን ኩርዝ ፓርቲ 38 በመቶ ያገኘ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር 31 በመቶ ነበር ያገኘው፡፡

የእርሱ ተቀናቃኝና ተጣማሪ የሆነው የሶሻል ዲሞክራቱ ፓርቲ 17 በመቶ ድምጽ ማግኘቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አሁን የተገኘው ውጤትም የወግ አጥባቂ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ጥምር መንግሥት ለመመስረት እና ለመመምራት የሚያስችለዉ ነጥብ መሆኑም በዘገባው ተመላክቷል፡፡

ይህ ምርጫ የተካሂደው ባለፈዉ ግንቦት ወር የኦስትርያ ተጣማሪ መንግሥት የወግ አጥባቂዉ ፓርቲ « ÖVP » እና ቀኝ ክንፍ ፓርቲ « FPÖ» ክፍፍል ገብቶ በመፍረሱ ነበር።

የኦስትርያዉ ወግ አጥባቂ « ÖVP » ፓርቲ የቀድሞ ፕሬዚደንት ለምርጫ ዘመቻ ድጋፍ የሚዉል ገንዘብን ከሩስያ ለመቀበል ሲያመቻቹ የሚያሳይ ቪዲዮ መገኘቱን ተከትሎ ጥምሩ መንግስት መፍረሱም አይዘነጋም፡፡

ትላንት በተካሄደዉ የፓርላማ ምርጫ 6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሕዝብ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የኦስትርያ ምክር ቤት በሃገሪቱ መራሔ መንግሥት ሰበስትያን ኩርዝ ላይ ባሳለፈዉ የመተማመኛ ጥያቄ፤ በቂ ድምፅን ባለማግኘታቸዉ፤ ኦስትርያ ዳግም የፓርላማ ምርጫ እንድታደርግ መወሰኑ ይታወቃል።

ፕሬዘዳንት ሰባስቲያን ኩርዝ በጥቅምት ወር 2011 ዓ.ም ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *