በቦሌ ብራስ አካባቢ ባለው የደመራ የባህል ምግብ ቤት አስተናጋጆች ተጣልተው የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ተገለጸ

በቦሌ ብራስ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የደመራ የባህል ምግብ ቤት የመስተንግዶ ሰራተኞች መካከል በተፈጠረ የግል ጸብ አንድ ሰው ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም ከአይን እማኞች እንዳረገጋጠው ጸቡ የተፈጠረው በምግብ ቤቱ ሁለት አስተናጋጆች መካከል ነው።

አንዱ አስተናጋጅም በደረሰበት የስለት ጥቃት ወደ ብራስ ሆስፒታል ተወስዶ ህይወቱን ለማዳን ርብርብ ቢደረግም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም።

ድብደባውን የፈጸመው ግለሰብ ለማምለጥ የሞከረ ቢሆንም በአካባቢው ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል።

በዳንኤል መላኩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *