ኢትዮጵያ ለ1 ሺህ የጎረቤት ሀገራት ዜጎች ነፃ የትህርት ዕድል ሰጠች

ኢትዮጲያ በየዓመቱ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ነፃ የትምህርት ዕድል የምትሰጥ ሲሆን ዕድሉን የሚያገኙ ተማሪዎች ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን አውቀናል፡፡

በ2012 ዓመት ኢትዮጲያ ለ6 ጎረቤት ሀገራት 1ሺ ተማሪዎች ነፃ የትምርት ዕድል ሰጥታለች ተብሏል፡፡

ተማሪዎቹ የትምህርት ዕድሉን በቅድመ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ማግኘታቸውን በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በዓለም አቀፋዊነት አጋርነት እና ስኮላርሺፕ ዳይሬክተር አቶ ምትኩ በሬቻ ነግረውናል፡፡

ባለፈው 2011 ዓመት ለ600 ተማሪዎች ነጻ የትምህርት እድል የሰጠች ሲሆን በ2012 ዓመት ደግሞ ለ1 ሺህ ዜጎች የትምህርት እድል ሰጥታለች፡፡

የነፃ ትምህርት ዕድል ለጎረቤት ሀገራት መሰጠቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ያጠናክረዋል ኢትዮጲያ በምስራቅ አፍሪካ ያላትን ተሰሚነትንም ያጎላል ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ደቡብ ሱዳን፣ ሰማሊያ ፣ ጅቡቲ እና ኤርትራ ዜጎች የነፃ የትህርት ዕድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ሀገራት ናቸው፡፡

በትግስት ዘላለም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *