የኤካ ኮተቤ የአዕምሮ ህክምናና አጠቃላይ ሆስፒታል ተመረቀ

ሆስፒታሉ ዛሬ ረፋድ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተመርቋል።
የጤና ሚኒስትር በአዲስ አበባ ከተማ ያስገነባው የአዕምሮ ህክምና እና አጠቃላይ ሆስፒታሉ ካሉት 350 አልጋዎች ውስጥ 175ቱ አልጋዎች ለአዕምሮ ህሙማን ህክምና ይውላሉ ተብሏል።

የኤካ ኮተቤ የአዕምሮ ህክምና እና አጠቃላይ ሆስፒታል በ350 የጤና ባለሙያዎች እና 174 ድጋፍ ሰጪ አስተዳደር ስራተኞች ከሚያዚያ 2009 ዓ.ም ጀምሮ የህክምና አገልግሎትም በመስጠት ላይ ይገኛል።

ሆስፒታሉ ስራውን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአእምሮ ህክምና 28 ሺህ 624 ታካሚዎች እንዲሁም በጠቅላላ ህክምና ዘርፍ ደግሞ 87 ሺህ 405 ታካሚዎች በአጠቃላይ 116 ሺህ 029 ታካሚዎች የህክምና አገልግሎት ሰጥቷል።

የቅዱስ አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አካል የሆነው የኤካ ኮተቤ የአዕምሮ ህክምና እና አጠቃላይ ሆስፒታል ግንባታው ሚያዝያ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ነበር የተጀመረው።

በደረሰ አማረ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *