Author: Ethio

14 Aug by Ethio

ቻይና የሆንግ ኮንግ ተቃውሞ ሰልፈኞችን ሽብርተኞች ናቸው አለች

በሆንግ ኮንግ የሚገኘው የቻይና ቢሮ እንዳለው ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጸረ መንግስት ናቸው ከሽብርተኞች የተለዩ አይደሉም ብሏል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው የቻይና ጦር ወደ ሆንግ ኮንግ መጠጋቱን ጠቅሰው ቻይና ጉዳዩን ሰከን ባለ መንገድ እንድትመለከተው ጠይቀዋል ፡፡ መቀመጫውን በቤጂንግ ያደረገው የሆንግ ኮንግ እና ማካኡ ጉዳዮች ቢሮ መረን የለቀቀ ብጥብጥ እና ግጭት በህጉ መሰረት ተገቢውን ቅጣት ሊያገኝ ይገባል […]
14 Aug by Ethio

በኒውዝላንድ ከሰው ልጅ ክብደት ጋር ተቀራራቢ የሚሆን ፔንግዊን ተገኘ

የትልቅ በረዶ ግግር ተንሳፋፊው ፔንግዊን የሰውን ቁመና ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ቅሪት አካሉ በኒውዝላንድ ተገኝቷል፡፡ የዚህ ፔንግዊን ቅሪተ አካል 1.6 ሜትር ይረዝማል፡፡ ይህም ማለት 5 ጫማ እርዝማኔ ያለው መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ክብደቱ 80 ኪሎ ግራም ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ከአቋቋሙ ጋር ተዳምረው የሰው አቋምና ቅርፅ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ ሰው መሰሉ ፔንጊውን ከ66 ና 56 ሚሊየን ዓመታት በፊት […]
14 Aug by Ethio

በአዲስ አበባ ለባለዕድለኞች ያልተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በቡድን በተደራጁ ወጣቶች ቁልፋቸው እየተሰበሩ መሆኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ቤቶች አስተዳደር በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ለባለዕድለኞችና ለልማት ተነሺዎች ቤት ሲያስተላልፍ ከ10 ዓመት በላይ ሆኖታል። ግንባታቸው የተጠናቀቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በየጊዜው በዕጣ ማስተላለፉም ይታወሳል። ቂሊንጦ፣ኮየፈጬ፣የካአባዶ፣ቦሌ ቡልቡላና ሌሎች ስፍራዎች ደግሞ በቅርብ የተገነቡ ቤቶች የሚገኙባቸው የግንባታ ሳይቶች ናቸው። ይሁንና በነዚህ አካባቢዎች ቤቶች ተገንብተው ለነዋሪዎች በህጋዊ መንገድ የተላለፉ ቢኖሩም ለነዋሪዎች ተላልፈው ያልተሰጡ ቤቶች […]
14 Aug by Ethio

ስቴፋኒ ፍራፓርት-‹‹በቴሌቪዥን የሚያዩኝ ልጃገረዶች /ሴቶች ሁሉ ነገር እንደሚቻል ያውቃሉ ››

አልቢትሯ ከፈረንሳይ ምርጥ ዳኞች አንዷ ናት ፡፡ ዛሬ በኢስታምቡል በሊቨርፑል እና ቼልሲ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ትመራለች፡፡  የሚጨበጨብላቸው ዳኞች ጥቂት ናቸው ፡፡ እነርሱን የሚያወድስ መልዕክት በስታዲየሞች መመልከት ብርቅ ነው ፡፡ ባለፈው ሚያዚያ የአሚዬ ደጋዎች ያደረጉት ብዙዎችን ያስገረመው ለዚያ ነው ፡፡ ስትራስቡርግን ካስተናገዱበት ጨዋታ ቀደም ብሎ የተለየ ነገር ፈጸሙ ፡፡በርግጥ አጋጣሚው ታሪካዊ ነበር ፡፡በፈረንሳይ ሊግ […]
13 Aug by Ethio

ዓለማችን በየዕለቱ 3 ሺህ ወጣቶችን እያጣች እንደሆነ የዓለም የጤና ደርጅት ገለጸ

የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳየው ከአጠቃላዩ 7 ነጥብ 2 ቢሊየን የዓለም ህዝብ ቁጥር 3 ቢሊየኑ እድሜአቸው ከ25 ዓመት በታች ናቸው። ይህ የወጣቶች ቁጥር ከአጠቃላዩ የህዝብ ቁጥር 47 በመቶውን ድርሻ ይይዛል፡፡ 1 ነጥብ 2 ቢሊየኑም ከ 10 እስከ 19 የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ ታዲያ ከነዚህ ወጣች መካከል ነው ዓለም በየቀኑ 3ሺ ወጣቶችን በሞት ትነጠቃለች የተባለው፡፡ […]
13 Aug by Ethio

ለኢቦላ ቫይረስ መከላከያ እየተሰጡ ካሉ መድኃኒቶች ውስጥ ሁለቱ የማዳን አቅማቸው ወደ 90 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገለጸ

ለኢቦላ ቫይረስ የሚሰጡ መድሀኒቶች ላይ በተደረገ ተከታታይ ሙከራ 2 መድሀኒቶች ላይ ቫይረሱን የመቋቋም መጠናቸው ማደጉን ተመራማሪዎች አደረግነው ባሉት ተከታታይ ምርመራ ለማወቅ ችለዋል፡፡ መድሃኒቶቹ በቅርቡ ቫይረሱን መቆጣጠር እና ማከም የሚቻልበት ደረጃ ላይ ይደርሳሉ ሲሉም ተስፋ ጥለውበታል፡፡ የቫይረሱ ስርጭት እየተፋጠነ ባለባት ዴሞክራቲክ ኮንጎ 4 መድሀኒቶች ለታማሚዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ከነዚያ ውስጥ REGN-EB3 እና mAb114 የተባሉት […]
12 Aug by Ethio

ለ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህጻናት የልደት ማስረጃ ወረቀት በነጻ ሊሰጥ ነው

በሃገራችን የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የተጀመረው ነሃሴ 30 2008 ዓ/ም ሲሆን እድሜያቸው ከ1 አመት በታች ከሆኑ ህጻናት ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት በዚሁ ሂደት ተመዝግበዋል፡፡ ባሳለፍነው ቅዳሜ ሁለተኛው የወሳኝ ኩነት ምዝገባና ስታቲስቲክስ ቀን በአዲስ አበባ ተከብሯል፡፡ በእለቱ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተገኙ ሲሆን ዘመናዊ አኗኗርን ለሚከተል ህዝብ ህጋዊ ምዝገባ ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ግለሰባዊ ማንነት […]
12 Aug by Ethio

ለ10 ሰዎች ሞትና ለበርካታ ዜጎች ጉዳት መንስኤ በሆነው በምእራብ ሀረርጌ ዞን ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ላይ የአመራሮች እጅ ነበረበት ተባለ

በቦርደዴ ወረዳ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር እና የሰዎች ህይወት ህልፈት ላይ የአመሮች እጅ እንደነበረበት ሰምተናል፡፡ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከወረዳው ሊቀመንበር ጀምሮ የተለያዩ አመራሮች፣ የቦርደዴ ወራዳ ወንጀል መከላከል ፖሊሶች ጭምር በድርጊቱ ተሳትፈው ነበር ብለዋል፡፡ በወረዳው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት ያደረሱ እንዚህ አካላትን ጨምሮ 7 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር […]
9 Aug by Ethio

ቶጎ ሰላማዊ ሰልፎችን የሚከለክል አዲስ ህግ አወጣች

በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ቶጎ እየታየ ያለውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ፓርላማው የተቃውሞ ትዕይንተ ህዝብ ላይ ተጨማሪ ገደብ የሚጥል ህግ አፅድቋል፡፡ መንግስት ህጉ ማስፈለጉ የሀገሪቷን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ነው ያለ ሲሆን ተቃዋሚዎች ግን እንደ አውሮፓውያኑ ከ1967 ጀምሮ የፕሬዝዳንትነቱ ስልጣን ከአንድ ቤተሰብ አለመውጣቱ ያስቆጣቸውን ተቃውሞ ሰልፈኞች ለማፈን ያቀደ ህግ ነው እያሉ ነው፡፡ በአዲሱ ህግ መሰረት በዋና ዋና አውራ […]
9 Aug by Ethio

የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ከደረጃ ሐ ግብር ከፋዬች 3.8 ቢሊዮን ብር መሰብሰብን ገለጸ

በባለስልጣኑ ታክስ ጉዳዬች ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዬሴፍ ግርማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት ከደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 3.8 ቢሊዬን ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡ በዘንድሮው አመት በርካታ ግብር ከፋዬች በወቅቱ ግብራቸውን በማሳወቅና በመክፈል የሚበረታታ ተግባር ፈጽመዋልም ብለውናል፡፡ በሲስተም ችግር ምክንያትና በግል ምክንያቶች ግብራቸውን ያልከፈሉ ጥቂት ደንበኞች መኖራቸው አይቀርም ያሉን ምክትል ዋና […]