ዜናዎቻችን

ቢቢሲ እንዳወራው ጥሪው የቀረበው  ዋሽንግተን የሚገኘው  የደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት  ከሰሜን ኮሪያ  የተላከውን ደብዳቤ አቅርበዋል፡፡ እንደ ኃላፊዎቹ ከሆነ ኪም የኒውክለር ፕሮግራሙን  እስከ  መዝጋትም የሚያደርስ ቁርጠኝነት አሳይተዋል ብለዋል መልዕክተኞቹ፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራንምፕ የሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ለኒውክለር ድርድር ያሳዩትን ፍላጎት አድንቀዋል፡፡ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ሙን ጃን ኢን  ውይይቱን የሰላም ድርድር ብለውታል፡፡ ይህ ከወራት ማስፈራሪያ እና እንቢተኝነት […]

አፍሪካ ኤድስ ኢኒሼቲቭ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ለሴት ተማሪዎች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ሰርቶ የኢንተርኔት አገልግሎት በበቂ ሁኔታ እንዲያገኙ ማዕከሉን በማስመረቅ ክፍት አድርጓል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በማዕከሉ ምርቃት ወቅት እንደተናገሩት ዩ ኤን ኤፍ ፒ ኤ የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት ከአፍሪካ ኤድስ ኢኒሼቲቭ ጋር በጋራ በመሆን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለማብቃት እየተገበራቸው ያለውን ፕሮግራሞች […]

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደቀ። ምክር ቤቱ በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ በምክር ቤቱ ከተገኙ 490 አባላት መካከል በ346 ድጋፍ፣ በ88 ተቃውሞ እና በ7 ድምጸ ተአቅቦ አፅድቆታል። የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ.ም

February 27, 2018

የካቲት 20 ቀን 2010 ዓ.ም   የኢትዮጵያውያን የመቃብር ስፍራዎች የአዉሮፓዉያን ባህል የሚያንጸባርቁ ናቸዉ ተባለ፡፡   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን መካነ መቃብሮች ላይ ሀዉልት ከማሰራት ይልቅ ቤቶችን በመስራት ቤት አልባ ድሆችን እንዲኖሩበትማድረግ የተሻለ ነዉ ብላለች፡፡  በቤተክርስትያንዋ በመንበረ ፓትሪያሪክ ዋና ስራ  አስኪያጅና የደቡብ ትግራይ ማይጨው አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አባ ዴስቆሮስለኢትዮኤፍኤም እንደተናገሩት መካነ መቃብራት ላይ ትልልቅ ሀውልቶችን በድንጋይ መካብ ከምልክት ባለፈ ቢገነባም ባይገነባም ከነብስ ድህነት ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም ብለዉናል፡፡ ሊቀ ጳጳሱ ሀዉልት የመቃብር ቦታ የአውሮፓውያን ባህል ነዉ፡፡ ከሰራነዉም ለሌሎች መጠለያ የሚሆንበት መንገድ ቢኖር መልካም ነዉ ይላሉ፡፡ በትዉልዱም እንዳለ የአዉሮፓን ባህል መቀበል ዝንባሌ አለ ይህም ምንም አይጠቅመንም   ምክንያቱም […]

ሼፍ አቶ እስክንድር የጾም ወቅት አመጋገባብ ስርዓት ቢዘወተር ለጤና ጥሩ ይላሉ፡ በሀገራችን ያለው የፆም ወቅት አመጋገብ ጤናማ ነዉ በጾምም ወቅት ልናዘወትራቸዉ ይእንደሚገባ ሼፉ ለኢትዮኤፍኤም ተናግረዋል፡፡ አትክልቶችና ፍራፍሬዎችን በመደባለቅና በጁስ መልክ በማዘጋጀት አማራጭ የፆም ምግቦችን ማዘጋጀት እንሚቻል ከሼፍ እስክንድር ሰምተናል፡፡ 1 ማንኪያ ማር፣ 2 ራስ ካሮት፣1 ራስ ሎሚ ከግማሽ ሊትር ውሃ ጋር ቀላቅሎ በመፍጨት በቀላሉ መጠቀም […]

የካቲት 20 ቀን 2010 ዓ.ም   ግብጽ ያለምክንያት ተቃዋሚዎችን ማሰራን ታቁም ሲል ሂውማ ራይትስ ዋች ጠይቋል፡፡ ተቋሙ የግብጽን ባስልጣኖች ተቀናቃኝ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ህጋዊ ባልሆነ አግባብ በተደጋጋሚ ማሯን እንድታቆም ያሳሰበ ሲሆን በዚህ መልኩ ሰዎቹን ከመርጫ ውጭ እንዲሆኑ ማድረግም ትክክል አይደለም ሲልም ድርጊቱን አውግዟል፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር ተቋሙን ጠቅሶ እንዳስነበበው ግብጽ በ2012 ፕሬዝዳንታዊ እጩ የነበሩትን አብደል […]

የካቲት 20 ቀን 2010 ዓ.ም     ኔታናያሁ የምርመራቸው ቀን እንዲራዘምላቸው ጠየቁ፡፡ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤናሚን ኔታናያሁ ፖሊስ በሁለት የሙስና ወንጀሎች ጥያቄ ሊያቅርብላቸው የያዘውን ቀነ ቀጠሮ እንዲያራዝምላቸው ጠይቀዋል፡፡ የሀገሪቱ ራዲዮ ጣቢያ ካን እንደዘገበው ኔታናያሁ በሚቀጥለው ቅዳሜ ወደ አሜሪካ ጉዞ ስላለብኝ ባይሆን ከጉዞ መልስ ልትጠይቆኝ ትችላላችሁ ብለዋል፡፡ የእስራኤል ፖሊስም በጠቅላይ ሚነስትሩ ጥያቄ በመስማማት ኔታናያሁ ከአሜሪካ ሲመለሱ […]

የካቲት 20 ቀን 2010 ዓ.ም     ትራምፕ በመሳሪያ ህግ ላይ ሊወያዩ ነው፡፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሁሉም አቅጣጫ ግፊት ሲበዛባቸው ከሀገሪቱ ህግ አውጭዎች ጋር ቁጭ ብለው በመሳሪያ አጠቃቀም ዙሪያ ሊመክርሩ ነው ተብሏል፡፡ ሮይተርስ እነደዘገበው ፕሬዝዳንቱ ከሪፓብሊካንና ከዴሞክቶቾ የህግ ሰዎች ጋር ነው ውይይቱን የሚያካዱት፡፡ የኋይት ሀውስ የፕሬስ ሀላፊ ሳራ ሳንደርስ  ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከህግ አውጭዎቹ ጋር […]

የካቲት 20 ቀን 2010 ዓ.ም   ሱዳንና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ስብሰባ እያደረጉ ነው፡፡ ካርቱም ላይ በተጀመረው የኢትዮጵያና የሱዳን ሁለተኛው ወታራዊ ስትራቴጂ ፎረም ላይ ለመሳተፍ ኢትዮጵያን ወክለው ወደ ቦታው ያቀኑት  የመካላከያ ሰራዊት ምክትል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አደም ሞሀመድ ናቸው፡፡ ሱዳን ትሪቢዩን እንደዘገበው ፎረሙ ትኩረት የሚያደርገው ሁለቱ ሀገሮች በወታደራዊ፣ በደህንነትና በፖለቲካዊ መስኮች ያሏቸውን የጋራ ፍላጎቶች ለማሳካት በሚያግዙ  ጉዳዮች […]

(የካቲት 19 ቀን 2010 ዓ.ም)   የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እየገመገመ ነዉ፡፡ 36ኛዉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋማዊ ለዉጥ ምክር ቤት ጉባኤ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተናጋጅነት ዛሬ ተጀምሯል፡፡፡ ጉባኤዉ በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በየ 3 ወሩ የሚካሄድ ነዉ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አሰማሀኝ አስረስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ጉባኤዉ በዩኒቨርስቲዎች የተሰሩ ስራዎች የሚገመገሙበትና […]


LIVE – የቀጥታ ስርጭት

Ethio FM Radio Live

Current track
TITLE
ARTIST