ዜናዎቻችን

የፖለቲካ  ፓርቲዎች  በብሔራዊ  መግባባት  ላይ  ለመደራደር  ውይይት  አካሄዱ፡፡

የፖለቲካ  ፓርቲዎቹ  በነበራቸው  ድርድር  በባለሙያዎች  ተዘጋጅቶ  በሚቀርበው  የፀረ  ሽብር  ህግ  ላይ  ውይይት  ለማድረግ ቀጠሮ  ቢይዙም  የሚዘጋጀው  ሰነድ  ባለማለቁ  ነው  በብሔራዊ  መግባባት  የድርድር  አጀንዳ  ላይ  ቅድመ  ድርድር  ወይይት ያደረጉት። 11ዱ  የፖለቲካ  ፓርቲዎች  የብሄራዊ  መግባባት  በፖለቲካ  ፓርቲዎች  ብቻ  የሚታጠር  ባለመሆኑ  በምን  መልኩ  መደረግ አለበት  የሚለውን  የሚሰራ  ኮሚቴ  እንዲቋቋም  ሀሳብ  አቅርቧል። በዚህ ሀሳብ  የተስማሙ  የፖለቲካ  ፓርቲዎች  ቢኖሩም  የገዳ  ሰርዓት፣  መኦዴፓ  እና  ኢሰዴፓ  ለድርድር  ባቀረብነው  ሀሳብ ላይ  በህገ  ደንቡ  መሰረት  ድርድር  መደረግ  አለበት  የሚል   ሀሳብም  አንስተዋል። ኢህአዴግም በተወካ አዳረዳሪዉ አምባሳደር ደግፌ ቡላ አማካኝነት…

ሳልቫ ኪር ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በደቡብ ሱዳን ሰላም ዙሪያለመምከር ነው ወደ ኢትዮጵ የመጡት፡፡ የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ኃይሎች ከአሁን ቀደም የሁለተኛውን ዙር የሰላም ሂደት ማሳለጫ ድርድር አዲስ አበባ ውስጥአድርገው ነበር። እነዚህ ተፋላሚ ወገኖች በተደጋጋሚ እየፈረሙ የሚጥሱትን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያከብሩም ማረጋገጫሰጥተዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት እንዳለው…

አልሲሲ ቃለ መሐላ ሊፈጽሙ ነው፡፡

የግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ለሁለተኛ ጊዜ በሥልጣን የሚቆዩበትን ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ። አልአህራምጋዜጣ እንደዘገበው የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዓቱ በፈረንጆቹ ሰኔ 2 ይፈጸማል። ባለፈው ኅዳር በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አልሲሲ 97 ከመቶ ድምጽ በማግኘት ነበር ያሸነፉት። በኅዳሩ ምርጫ አልሲሲ ማሸነፋቸው ከውድድር በፊትም ቢሆን እንዲጠበቅ ያደረገው ተፎካካሪያቸው እምብዛምም በሕዝብዘንድ የማይታወቁ የነበሩና ወደ ውድድር ከመግባታቸው በፊትም የአልሲሲን ዳግም መመረጥ በይፋ ይደግፉ የነበሩ ሰውበመሆናቸው ነው። የአልሲሲ ተቀናቃኞች ሰውየው አፋኝና አምባገነን ናቸው ሲሏቸው ደጋፊዎቻቸው በአንጻሩ ለአገሪቱ መረጋጋትንአምጥተዋል ብለው ያሞካሿቸዋል።