Featured

በዚህ ምክንያም ከፍተኛ የሆነ የህክምና መስተጓጎል ያስከተለ ሲሆን ባለፉት ሶስት ሳምንታት ምንም አይነት የአጥንት ቀዶ ህክምና መስጠት አልተቻለም፡፡ በተለይ የአጥንት ቀዶ ህክምና በሚሰጥበት ህንፃ ለ20 ቀናት ምንም አይነት የመብራት አቅርቦት እንዳልነበር አንድ ስማቸዉ እንዳይገለፅ የፈለጉ የሆስፒታሉ ሀኪም ለኢት ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡ በሀገራችን በተለይም በአዲስ አበባ በሚከሰተዉ አስከፊ የመኪና አደጋና በተለያዩ የመዉደቅ አደጋዎች የሚፈጠሩ አጋጣሚዎች በቁጥር […]

የሀገሪቱ መንግስት ዘመም የሆነዉ MENA የተባለዉ የዜና ወኪል እንደዘገበዉ ሀገሪቱ ለሀይል ሴክተሩ የምታርገዉን ድጎማ ልታቆም በመወሰኗ ነዉ ከፍተኛ የአገልግሎት ክፍያ የምታስቀምጠዉ፡፡ ግብጽ ከአለም ባንክ የተበደረችዉ 12 ቢሊየን ዶላር በሀይል ሴክተሯ ላይ የምታደርገዉን ድጎማ እንድታቋርጥ አስገድዷታል፡፡ አዲሱ ዋጋም በመጭዉ ሀምሌ ወር ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በኤሌክትሪክ ሚንስትሩ አማካኝነት በሚሰጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ይሆናል፡፡ መንግስት ያለበትን የገንዘብ እጥረት […]

ዋሽንግተን እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከታይዋን ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነቷን  ብታቋርጥም የትንሿ ደሴት ሁነኛ አጋር ከመሆን ያገዳት ነገር የለም፡፡ ይሄ ድርጊት ደግሞ ቻይናን ያስቆጣል፡፡ ምክንየቱም ቤጅንግ አንዲት ቻይና በሚለው ፖሊሲዋ ታይዋን ይዞታየ ናት ብላ ስለምትከራከር ነው፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው የታይዋኗ ፕሬዝዳንት የአሜሪካን ተነሳሽነት አድንቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ ነገሩ ታይዋን ግዛቴ ናት በምትለው ቻበይናና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደባሰ ውጥረት […]

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮሪያው አቻቸው በዛሬው ዕለት በሲንጋፖር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ኪም ጆንግ ኡን የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ ሁለቱ መሪዎች ያደረጉትን ውይይት አስመክልቶ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ይህ ነገር ብዙዎችን ያስደስታል፤ ምክንያቱም የሁለቱ ሀገሮች ጉዳይ ለዓለም ስጋት ነበር ሲሉ ብለዋል፡፡ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በበኩላቸው፥ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ያደረኩት ውይይት ታሪካዊ እና እዚህ ለመድረስም ብዙ ውጣ ውረዶች የታየበት ነው ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

መንግስትበየመን የባህር ጠረፍ የደረሰን የጀልባ አደጋ አስመልክቶ ወደ ስፍራው ሰዎችን በማሰማራት፣ በአካባቢውየሚገኙ ኤምባሲዎቻችንን በማንቀሳቀስ እና የመን እና አዲስ አበባ የሚገኘው የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ጋርበመሆን አደጋውን በቅርበት ሲከታተለው እንደነበር አስታውቋል፡፡ በተደረገው ክትትልም 46 ያህል ዜጎቻችን በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን እንዳጡ አስታውቋል። መንግስት ከተባበሩት መንግስታት የፍልሰት ድርጅት እንዲሁም ከአደጋው የተረፉ ወገኖች ጋር ባደረገው ክትትልም 100ያህል ኢትዮጵያውያንን የጫነች ጀልባ ከቦሳሶ ሶማሊያ ተነስታ ስትጓዝ ካደረች በኋላ ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ.ም የመንየባህር ጠረፍ ላይ ስትደርስ በደረሳባት አደጋ 46 ሰዎች ሲሰጥሙ 15 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ብሏል፡፡ ቀሪዎቹ ከአደጋው የተረፉ 39 ወገኖቻችን በአከባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እንዲሁም ከዓለም አቀፍየፍልሰት ድርጅት ጋር በመተባበር የመን ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ይህን አሳዛኝ አደጋ መከሰቱ የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውር እንቅስቃሴው ምን ያህል ውስብስብና አስቸጋሪ የወንጀል ድርጊት እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ነው መንግስትም ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብሏል፡፡ ጀልባዋ የመስመጥ አደጋ የደረሰባት ከመጫን አቅሟ በላይ የሆነ ተሳፋሪ ይዛ በመጓዟ እና በዚህ ጉዞ ወቅትም ተሳፋሪዎቹከጸጥታ ሀይሎች እና ከሰው እይታ ለመራቅ በማሰብ ከየብስ አቅራቢያ ርቀው ይጓዙ ስለነበር የህይወት ማትረፍ ሙከራውውጤት እንዳላመጣ ከአለም አቀፍ አጋሮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ሲል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አሰታውቋል ፡፡

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር በየመን ባለው የደህንነት ችግር ምክንያት ነዉ ያስወጣዉ፡፡ አልጀዚራ እንዳወራዉ፣በአሁን ወቅት የቀይ መስቀል ማህበር በርካታ የውጭ ዜጎችን ጨምሮ 450 የሚሆኑ ሰራተቾች በየመንአሰማርቷል፡፡ የእርዳታ ድርጅቱ የምግብ፣ የውሃ እና ሌሎች ጤና ነክ አገልግሎቶችን ለማቅረብ በሀገሪቱ የሚገኙ ሀይሎች ዋስትናእንዲሰጧቸው ጠይቋል። ይህም ዋስትና ለተጎዱ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ እንዳይቋረጥም ያስችላል ተብሏል። የቀይ መስቀል ማህበርም በግጭቱ ተሳትፎ ከሚያደርጉት ሁሉም አካላት አስተማማኝ፣ ጠንካራ እና ተግባራዊ የሚደረግዋስትና ማግኘት ከቻለ ለየመንያውያን የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የቀይ መስቀል ማህበር በችግሩ ምክንያት በአሁን ወቅት እንቅስቃሴው እንደተገደበ እና ለአደጋ እንደተጋለጠም አስታዉቋል፡፡ በሀገሪቱ ባለው ጦርነት ሳቢያ 10ሺህ ያህል ዜጎች ህይወታቸውን ሲያጡ፣ 40 ሺህ የሚሆኑት የመቁሰል አደጋ እንዳጋጠማቸውዘገባዉ ጠቁሟል፡፡

ከኮተቤ-ካራ የሚያወጣው የአስፓልት መንገድ እንደገና እንደ አዲስ በመሰራት ላይ በመሆኑ፣ ከወሰን ወደ ካራ በሚያወጣው ተለዋጭ መንገድ ላይ ከፍተኛ መጨናነቅን እየፈጠረ ነዉ፡፡ በዚህም ሰዓታትን በመንገድ ላይ ለማሳለፍ የተገደዱት ነዋሪዎችና አሽከርካሪዎች፣ ችግሩ ለከፍተኛ እንግልት ዳርጎናል ብለዋል፡፡ ከ 15 ዓመት በላይ ታክሲ እንዳሽከረከረ የነገረን አቶ ለገሰ ገብረ-ፃዲቅ፣ የኮተቤው መንገድ ግንባታው ከተጀመረ በኋላ፣ ከወሰን ወደ ካራ የሚወስደው መንገድ ላይ […]


LIVE – የቀጥታ ስርጭት

Ethio FM Radio Live

Current track
TITLE
ARTIST